2008 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ U-17 የጥሎ ማለፍ ውድድር በ14 ክለቦች መካከል ቅዳሜ ተጀምሯል፡፡
12 ክለቦች የመጀመርያውን ዙር ጨዋታ ያደረጉ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና እና ሀዋሳ ከተማ በቀጥታ ወደ ሩብ ፍፃሜ እንዲያልፉ ተደርጓል፡፡
ቅዳሜ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ኢትዮ ስፖርት አካዳሚ ከ አፍሮ ፅዮን ያደረጉት ጨዋታ በመደበኛው ክፍለ ጊዜ 1-1 በመጠናቀቁ በተሰጠው የመለያ ምት አፍሮ ፅዮን 5-3 አሸንፏል፡፡
እሁድ አዳማ ላይ አዳማ ከተማ ደደቢትን አስተናግዶ በመደበኛው ክፍለ ጊዜ ያለግብ በመጠናቀቁ በተሰጠው የመለያ ምት ደደቢት 5-3 አሸንፏል፡፡
አዲስ አበባ ስታድየም ላይ በ09:00 በመደበኛ ክፍለ ጊዜ በተጠናቀቀው ብቸኛ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅዱስ ጊዮርጊስን 3-2 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል፡፡
11:00 ላይ ኤሌትሪክ ከ አአ ከተማ መደበኛው ክፍለ ጊዜ 1-1 በመጠናቀቁ በተሰጠው የመለያ ምት ኤሌትሪክ 5 – 4 አሸንፏል፡፡
ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡና ከመከላከያ ሊያደርጉ የነበረው ጨዋታ ሲዳማ ቡና ከአቅም በላይ ችግር ሳይሳተፍ በመቅረቱ ፎርፌ ለመከላከያ ተሰጥቷል፡፡
ሶዶ ላይም በተመሳሳይ በወላይታ ድቻ እና ሐረር ሲቲ መካከል መካሄድ የነበረበት ጨዋታ ሐረር ሲቲ ከአቅም በላይ ባጋጠመው ችግር ምክንያት ለወላይታ ድቻ ፎርፌ ተሰጥቷል ፡
በውጤቶቹ መሰረት ወላይታ ድቻ ፣ መከላከያ ፣ ኤሌክትሪክ ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ደደቢት ፣ አፍሮ ፅዮን ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ሀዋሳ ከተማ ወደ ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀሉ ክለቦች ሆነዋል፡፡
የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ ሲካሄዱ ቅዳሜ በ9:00 ኢትዮዽያ ቡና ከ መከላከያ ፣ በ11:00 ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአአ ስቴዲዮም ይጫወታሉ፡፡
እሁድ 11:00 ላይ ኤሌክትሪክአ ከፍሮ ፅዮን ሲጫወቱ ሀዋሳ ከተማ ከ ደደቢት ጨዋታ የሚያደርጉበት ቀንና ቦታ ወደ ፊት ይገለፃል፡፡