በ7 ዞኖች ተከፍሎ ሲካሄድ የቆየው የ2008 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ ሊጠናቀቅ የአንድ ሳምንት እድሜ ቀርቶታል፡፡ ከቅዳሜ ጀምሮ በሚደረጉ ጨዋታዎችም ፍፃሜውን ያገኛል፡፡
ውድድሩ በዚህ ሳምንት እንዲጠናቀቅ ፕሮግራም ወጥቶለት የነበረ ቢሆን ከየዞኖቹ በተለያየ ምክንያት ጨዋታ ያላደረጉ ቡድኖች በዚህ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታቸውን አከናውነው በቀጣይ ሳምንት ሁሉም ዞን እኩል እንዲጠናቀቅ ተደርጓል፡፡
እሁድ በተደረጉ ተስተካካይ ጨዋታዎች የተመዘገቡት ውጤቶች ይህንን ይመስላሉ፡-
ዳባት ከተማ 0 – 0 ደባርቅ ከተማ
ለገጣፎ 0 – 0 ቡታጅራ ከተማ
ጋርዱላ 0 – 0 ዲላ ከተማ
ዱከም ከተማ 4 – 1 መቂ ከተማ
የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች ፕሮግራም
ሰሜን ምዕራብ ዞን ምድብ ለ
እሁድ ሰኔ 26 ቀን 2008
09፡00 ሶሎዳ አድዋ ከ ላስታ ላሊበላ (አድዋ)
09፡00 ዋልታ ፖሊስ ከ ትግራይ ውሃ ስራ (ውቅሮ)
09፡00 ሽረ እንዳስላሴ ከ ደሴ ከተማ (ሽረ)
ደቡብ ምዕራብ ዞን ምድብ ሀ
እሁድ ሰኔ 26 ቀን 2008
09፡00 ጋምቤላ ከተማ ከ ሚዛን አማን (ጋምቤላ)
09፡00 ከፋ ቡና ከ ዩኒቲ ጋምቤላ (ቦንጋ)
09፡00 መቱ ከተማ ከ አሶሳ ከተማ (መቱ)
ሰሜን ምዕራብ ዞን ምድብ ሀ
እሁድ ሰኔ 26 ቀን 2008
09፡00 ጎጃም ደብረማርቆስ ከ አዊ እምፒልታቅ (ደብረማርቆስ)
09፡00 አምባ ጊዮርጊስ ከ አማራ ፖሊስ (አምባ ጊዮርጊስ)
09፡00 ደባርቅ ከተማ ከ ዳሞት ከተማ (ደባርቅ)
እሁድ ሰኔ 26 ቀን 2008
09፡00 ሆለታ ከተማ ከ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ (ሆለታ)
09፡00 ወሊሶ ከተማ ከ ቦሌ ገርጂ ዩኒየን (ወሊሶ)
09፡00 አምቦ ከተማ ከ ጨፌ ዶንሳ (አምቦ)
ቀን እና ሰአት ወደ ፊት የሚገለፅ
አራዳ ክ/ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ (አበበ ቢቂላ)
ደቡብ ምዕራብ ዞን ምድብ ለ
እሁድ ሰኔ 26 ቀን 2008
09፡00 ወላይታ ሶዶ ከ ጎባ ከተማ (ሶዶ)
09፡00 ጋርዱላ ከ ጎፋ ባሪንቾ (ጋርዱላ)
09፡00 ዲላ ከተማ ከ ቡሌ ሆራ (ዲላ)
09፡00 ሮቤ ከተማ ከ አንባሪቾ (ሮቤ)
መካከለኛ ዞን ምድብ ሀ
እሁድ ሰኔ 26 ቀን 2008
09፡00 መቂ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ (መቂ)
09፡00 ቡታጅራ ከተማ ከ የካ ክ/ከተማ (ቡታጅራ)
ቀን እና ሰአት ወደ ፊት የሚገለፁ ጨዋታዎች
ልደታ ክ/ከተማ ከ ለገጣፎ ከተማ (አበበ ቢቂላ)
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከ ቱሉ ቦሎ (አበበ ቢቂላ)
ምስራቅ ዞን
ቅዳሜ ሰኔ 25 ቀን 2008
09፡00 ካሊ ጅግጅጋ ከ ወንጂ ስኳር (ጅግጅጋ)
እሁድ ሰኔ 26 ቀን 2008
09፡00 ኢትዮ ሶማሌ ፖሊስ ከ አሊ ሐብቴ ጋራዥ (ጅግጅጋ)
09፡00 ሐረር ሲቲ ከ መተሃራ ስኳር (ሐረር)
09፡00 ቢሾፍቱ ከተማ ከ ሞጆ ከተማ (ቢሾፍቱ)
ማስታወሻ
– የማጠቃለያ ውድድሩ በ16 ክለቦች መካከል የሚደረግ ሲሆን የት እንደሚደረግ አልታወቀም፡፡
– ከየዞናቸው 1ኛ እና 2ኛ የሚወጡ 14 ቡድኖች እንዲሁም በ3ኝነት የሚያጠናቅቁ ቡድኖች ነጥባቸው ካደረጉት ጨዋታ ጋር ተሰልቶ የተሻሉ ሁለት ቡድኖች ወደ ማጠቃለያው ያልፋሉ፡፡
– ከጎናቸው (Q) የተፃፈባቸው ወደ ማጠቃለያ ዙር ማለፋቸውን ያረጋገጡ ቡድኖች ሲሆኑ (R) የተፃፈባቸው ከብሄራዊ ሊጉ መውረዳቸውን ያረጋገጡ ቡድኖች ናቸው፡፡ (C) ደግሞ የዞኑ ቻምፒዮን መሆናቸውን ያረጋገጡ ናቸው፡፡
– በማጠቃለያ ውድድሩ ከ1-6 የሚወጡ ቡድኖች ወደ ከፍተኛ ሊግ ያልፋሉ፡፡