ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ፍፃሜ ፡ ደደቢት ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

የደደቢቷ አምበል ኤደን ሽፈራው የሊጉን ዋንጫ አነስታለች፡፡ የ2008 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግም በደደቢት ቻምፒዮንነት ተጠናቋል፡፡

1ኛ ደረጃ – ደደቢት
የወርቅ ሜዳልያ እና 100,000 ብር

2ኛ ደረጃ – ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የብር ሜዳልያ እና 75,000 ብር

3ኛ ደረጃ – መከላከያ
የነሀስ ሜዳልያ እና 50,000 ብር

የስፖርታዊ ጨዋነት ዋንጫ – መከላከያ

ኮከብ አሰልጣኝ – ፍሬው ኃ/ማርያም (ደደቢት)
-15,000 ብር ተሸልመዋል፡፡

ኮከብ ተጫዋች – ሽታዬ ሲሳይ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
– 15,000ብር ተሸልማለች፡፡

ከፍተኛ ግብ አግቢ – ሎዛ አበራ (10 ግቦች)
– 15,000ብር ተሸልማለች፡፡

ኮከብ ግብ ጠባቂ – ሊያ ሽብሩ (ደደቢት)
-10,000 ብር እና ዋንጫ ተሸልማለች፡፡

የዞን ከፍተኛ ግብ አግቢዎች
በየዞኑ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ የሆኑት ሎዛ ፣ አይናለም አሳምነው እና ተራማጅ ተስፋዬ እያንዳንዳቸው የ5000 ብር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

የዞን አሸናፊዎች
የማከላዊ-ሰሜን ዞን አሸናፊ – ደደቢት የደቡብ ዞን አሸናፊ – ሀዋሳ ከተማ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

የአመቱ ኮከብ ዳኞች
ዋና ዳኛ – ሊዲያ ታፈሰ
ረዳት ዳኛ – ወጋየሁ ዘውዴ

11:26 የዕለቱን ጨዋታ ለመሩት ዳኞች እና ኮሚሽነር የሜዳልያ ሽልማት እየተበረከተላቸው ይገኛል፡፡

11:23 በአሁኑ ሰአት ለውድድሩ መሳካት ድጋፍ ላደረጉ ተቋማት የምስጋና ሽልማት እየተሰጠ ነው፡፡


ደደቢት 2-0 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
31′ 58′ ሎዛ አበራ


ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በደደቢት 2-0 አሸናፊነት ተጠናቀ፡፡ የመካከለኛ-ሰሜን ዞን ቻምፒዮኑ ደደቢት የማጠቃለያው ውድድርንም በቻምፒዮንነት አጠናቋል፡፡

ቀይ ካርድ
90+2′
አልፍያ ጃርሶ ከዳኛ ጋር ሰጣ ገባ በመግባቷ በቀይ ካርድ ወጣች፡፡

ቢጫ ካርድ
90+2′
ሎዛ ብቻዋን ወደጎል እየሄደች ፅዮን ፈየራ ጠልፋ በማስቀረቷ በመጥለፏ የማስጠንቀቂያ ካርድተመልክታለች

ተጨማሪ ደቂቃ
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 6 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

86′ ረሂማ ዘርጋው ከ16:50 አክርራ የመታችው ኳስ ለጥቂት የጎሉን አግዳሚ ታኮ ወጣ፡፡

79′ ንግድ ባንክ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት እያደረገ ቢሆንም ጠንካራውን የደደቢት ተከላካዮችን አልፎ ጎል ለማስቆጠር ተቸግሯል፡፡

የተጨዋች ለውጥ ደደቢት
78′
ሰናይት ባሩዳ ወጥታ ዘለቃ አሰፋ ገብታለች፡፡

70′ ፅዮን ፈየራ ከቅጣት ምት የተመታው ኳስ ሲጨራረፍ ያገኘችውን ግልፅ የጎል አጋጣሚ አመከነች፡፡

ቢጫ ካርድ
68′
በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ሆን ብላ ሳትነካ ወድቃለች በሚል አልቢቴር ሊዲያ ለሽታዬ ቢጫ ካርድ አሳይታለች፡፡

67′ ሁኔታው ተመልካችን እያዝናና ይገኛል፡፡ በአሁኑ ሰአት ተጠግኖ ጨዋታው ተጀምሯል፡፡

64′ በቀኝ መስመር የሚገኘው የማዕዘን ምልክት ተሰብሮ በመጠገን ላይ በመሆኑ ጨዋታው ቆሟል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ባንክ
62′
እፀገነት ብዙነህ ወጥታ ትግስት ያደታ ገብታለች

60′ ከአአ የመጡ የደደቢት ደጋፊዎች በዜማ ጨዋታውን እያደመቁ ይገኛሉ፡፡

ጎልልል!!!!!
58′ ሎዛ አበራ የፍጹም ቅጣት ምቱን ወደ ግብነት ቀይራለች፡፡

ፍፁም ቅጣት ምት
56′
ፍጹም ቅጣት ምት ለደደቢት ተሰጥቷል፡፡

55′ ሎዛ በተደጋጋሚ ግብ ሊሆኑ የሚችሉ ኳሶች እያመከነች ትገኛለች፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀመረ፡፡

የእረፍት ሰአት የተጫዋች ለውጥ
ቅድስት ቦጋለ ወጥታ ዙለይካ ጁሃድ ገብታለች፡፡


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በደደቢት መሪነት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ደቂቃ ተጠናቆ 4ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

34′ ሽታዬ ሲሳይ የሚያስቆጭ አጋጣሚ አመከነች:: ከሊያ ጋር እንድ ለአንድ ብትገናኝም ግብ ጠባቂዋ አድናባታለች፡፡ ሊያ ድንቅ ግብ ጠባቂ መሆኗን እያሳየች ትገኛለች፡፡

ጎልልል!!!! ደደቢት
31′ ሎዛ አበራ ከሰናይት ባሩዳ የተሻገረላትን ኳስ በሚገባ ተጠቀማ ደደቢትን ቀዳሚ አድርጋለች፡፡

25′ ሎዛ አበራ ከርቀት የመታችውን ኳስ ዳግማዊት በቀላሉ ያዘችባት፡፡ ደደቢት ወደ ጨዋታው እየተመለሰ ነው፡፡

22′ ጨዋታው የፍፃሜ እንደመሆኑ በሁለቱም በኩል ተረጋግተው በሚገባ ኳሱን መጫወት ሲሳናቸው እያየን ነው፡፡

20′ እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የስፖርት ቤተሰብ እንዲሁም የፕሪሚየር ሊግ አሰልጣኞች እና ተጨዋቾች ጨዋታውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡

የተጨዋች ለውጥ – ደደቢት
14′ ዘቢብ ኀ/ስላሴ ወጥታ ነህምያ አበራ ገብታለች፡፡

13′ ረሂማ ዘርጋው ከሊያ ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝታ የሚያስቆጭ የጎል አጋጣሚ አመከነች፡፡

8′ ብሩክታዊት ግርማ በግራ መስመር አክርራ የመታችውን ኳስ ሊያ በቀላሉ ተቆጣጥራዋለች፡፡

5′ ኢትዮዽያ ንግድ ባንክ ጫና ፈጥሮ በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡

ተጀመረ!
የፍፃሜ ጨዋታው ተጀምሯል፡፡

ጨዋታው ሊጀመር ሁለቱ ቡድኖች ወደሜዳ በመግባት ከዕለቱ የክብር እንግዳ ጋር በመተዋወቅ ላይ ይገኛሉ፡፡


የደደቢት አሰላለፍ

24 ሊያ ሽብሩ

17 ዘቢብ ሃ/ስላሴ – 3 ወይንሸት ፀጋዬ – 4 መስከረም ካንኮ – 13 አስራት አበበ

16 አልፊያ ጃርሶ – 2 ኤደን ሽፈራው (አምበል) – 15 ሰናይት ቦጋለ

14 ሰናይት ባሩዳ – 12 ሎዛ አበራ – 11 ብርቱካን ገ/ክርስቶስ

ተጠባባቂዎች
ፍሬወይኒ ገብሩ
ትበይን መስፍን
ነህምያ አበራ
ኪፊያ አብዱልራህማን
ዮርዳኖስ መአዛ
ቤዛ ታደሰ


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ
1 ዳግማዊት መኮንን
20 ሀብታም እሸቱ – 12 ጥሩአንቺ መንገሻ – 20 ፅዮን እስጢፋኖስ – 17 እፀገነት ብዙነህ
14 ህይወት ደንጊሶ – 19 ቅድስት ቦጋለ – 16 ብሩክታዊት ግርማ

11 ሽታዬ ሲሳይ – 9 ረሂማ ዘርጋ (አምበል) – 10 ብዙነሽ ሲሳይ

ተጠባባቂዎች
ንግስት መአዛ
አዳነች ጌታቸው
እታፈራው አድርሴ
ብዙሃን እንዳለ
ዙሌይካ ጁሃድ
ቤዛዊት ተስፋዬ
ትዕግስት ያደታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *