“የስኬታችን ዋናው ሚስጥር መደማመጣችን እና መከባበራችን ነው ” አሰልጣኝ ፍሬው ኃ/ገብርኤል

የኢትየጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ትላንት ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ ደደቢትም የቻምፒዮንነቱን ዘውድ ደፍቷል፡፡

በዘንድሮው የውድድር ዘመን ደደቢትን በአሰልጣኝነት የተረከቡት አሰልጣኝ ፍሬው ኃ/ገብርኤል በመጀመርያ የውድድር ዘመናቸው ቻምፒዮን በመሆን ላለፉት 3 አመታት በሊጉ ከነገሰው ንግድ ባንክ ዋንጫውን መንጠቅ ችለዋል፡፡ የአመቱ ኮከብ አሰልጣኝ ተብለውም ተሸልመዋል፡፡

አሰልጣኝ ፍሬው ከድሉ በኋላ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር አጭር ቆይታ አድርገዋል፡፡


ውድድሩ እንዴት ነበር?

በጣም ደስ ይል ነበር ፤ ሁሉንም ጨዋታ በማሸነፍ ነው ቻምፒዮን የሆንነው፡፡ ለሀዋሳ ስፖርት አፍቃሪ ትልቅ ክብር አለን፡፡ ጥሩ የሚጫወቱትን እየደገፈ ፤ ሀገርን ወክለው የሚጫወቱትን እነ ሎዛን በዚህ መልክ ማነቃቃቱ ነገ ጥሩ ተጫዋቾችን ለማውጣት ጥሩ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብዬ አስባለው፡፡ በአጠቃለይ ውድድሩ ደስ የሚል ነበር፡፡

የዞኑ እና አጠቃላይ ቻምፒዮን ሆናችኀል…

ኦ እጅግ በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡ ለዚህ ስኬት ፈጣሪዬን በጣም አመሰግናለው፡፡

PicsArt_1467537422973

በመጀመርያ የውድድር ዘመንህ ዋንጫ አንስተሀል፡፡ የስኬትህ ሚስጢር ምንድን ነው?

እዚህ ክለብ ከመጣሁ ጀምሮ ያደረጉልኝ አቀባበል በጣም ደስ ይል ነበር፡፡ ያው እኔ ሲሪየስ ነኝ ፤ ስቆጣም ፣ ስናገርም በቀናነት ነበር የሚያዳምጡኝ፡፡  እንደ አሰልጣኝ እና እንደ ተጨዋች ሳይሆን እንደ ቤተሰብ ነበርን፡፡ ደግሞም ብዙም ለጥፈት የተጋለጡ አይደሉም፡፡ ስራቸውን በሚገባ ያውቃሉ ፤ ክብራቸውን ይጠብቃሉ፡፡ ለስኬታችን ዋናው ሚስጥር መዋደደችን ፣ መደማመጣችን እና መከባበራችን ነው፡፡

ሴቶችን ማሰልጠን እንዴት አገኘኸው?

ሴቶችን ማሰልጠን የመጀመርያዬ ይሁን እንጂ ወንዶችን ለረጅም ጊዜ በፕሮጀክት ሳሰለጥን ነበር፡፡ ዛሬ ለክለብና ለብሔራዊ ቡድን በመጫወት ላይ የሚገኙ ተጫዋቾችን አውጥቻለው፡፡ አለማያ ዩንቨርሲቲ በስፖርት ሳይንስ ድግሪ አለኝ ፤ በአጠቃለይ በስፖርቱ ጥሩ ልምድ አለኝ፡፡

ወደ ሴቶቹ ስመጣ ሴቶችን  ማሰልጠን ከባድ ነው፡፡ ሆኖም ለስራ የተዘጋጀ  ፈጣን ጭንቅላት አላቸው ፤ አልሸነፍ ባይነታቸው ይገርማል፡፡ ከዚህ በኋላ ሙያውን ስለምወደው  በሴቶች ላይ ጠንካራ ስራ ሰርቼ ለሀገሬም ለክለቤም ጥሩ ሰራ እሰራለው ብዬ አስባለው፡፡

PicsArt_1467537492034

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *