” ለኔ መስዋትነት ሲከፍሉ የነበሩ የቡድን አጋሮቼን ደጋግሜ ማመስገን እፈልጋለው ” ሎዛ አበራ

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ትላንት ፍፃሜውን ሲያገኝ ደደቢት ሎዛ አበራ ባስቆጠረቻቸው ሁለት ግቦች ታግዞ ንግድ ባንክን 2-0 በመርታት ቸምፒዮን ሆኗል፡፡

እጅግ የተሳካ የውድድር ዘመን ያሳለፈችው ሎዛ በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ማጠቃለያ በ6 ጨዋታ 10 ግቦችን አስቆጥራ ለሁለተኛ ተከታታይ አመት የኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ክብር ስትቀዳጅ በአጠቃላይ በሊጉ 57 ግቦችን በማስቆጠር ሪኮርድ ጨብጣለች፡፡

ሎዛ አበራ ከፍፃሜው ጨዋታ በኋላ ለሶከር ኢትዮጵያ የሰጠችውን አስተያየት እንዲህ አቅርበነዋል፡፡


ስለ ውድድሩ

በሀዋሳ በጣም አሪፍ ቆይታ ነበረን፡፡ በ15 ቀን ውስጥ ሁሉም ያላቸውን አቅም ያሳዩበት ነበር፡፡ እኛም እንደ ቡድን በህብረት በመጫወታችን አሸናፊ ሆነናል፡፡ ለዚህም ፈጣሪዬን አመሰግናለው፡፡

ኮከብ ጎል አስቆጣሪ መሆኗ የፈጠረባት ስሜት

በመጀመርያ የቡድን አጋሮቼን ማመስገን እፈልጋለው፡፡ እግር ኳስ የአንድ ሰው ስራ ስላልሆነ ሁሉም ለኔ መሰዋትነት ከፍለዋል፡፡ በተለይ ዛሬ ለኔ ነበር መስዋትነት ሲከፍሉ የነበሩት ፤ ለዚህም ደጋግሜ የቡድን አጋሮቼን ማመስገን እፈልጋለው፡፡ በግሌ በጣም ከፍተኛ የደስታ ሰሜት ተሰምቶኛል ፤  ቡድኔም ቻምፒዮን በመሆኑ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡

PicsArt_1467544628228

የጎል አነፍናፊነት ብቃት

ያው አጥቂ እንደመሆኔ መጠን ከኔ የሚጠበቅብኝን ስራ ለመስራት ሁሌም በጣም ዝግጁ ነኝ፡፡ የምችለውን ነገር ሁሉ አደርጋለው ፤ ብዙ ስህተቶች ሊኖሩብኝ  ይችላል፡፡ ነገር ግን ሁሌም ከኔ የሚጠበቅብኝን ለማድረግ ጠንክሬ በመስራቴ ይሆናል ስኬታማ የሆንኩት፡፡

ቀጣይነት

ያው ገና ብዙ አልሰራሁም ብዬ አስባለው፡፡ በቅርቡ ነው በትልቅ ደረጃ መጫወት የጀመርኩት ፤ ብዙ ነገር ማድረግ ይቀረኛል፡፡ ራሴን ጠብቄ ለሀገሬ ብዙ መስራት እፈልጋለው፡፡ ከሀገር ውጪ በመጫወት እራሴን ማሳየት እፈልጋለው፡፡ እነዚህን ለማድረግ አላማ ስላለኝ የምችለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ፡፡ ለዚህም ፈጣሪ ይረዳኛል፡፡

በመጨረሻም. . .

ይህን ቀን በጣም እጠብቀው ነበር፡፡ ክለቤ አሸናፊ በመሆኑ እኔ ደግሞ በኮከብ ግብ አግቢነት በማጠናቀቄ ደስ ብሎኛል፡፡ በጣም የተሳካ አመት አሳልፌያለሁ፡፡ ለዚህ ለረዱኝ ሁሉ ምስጋና አቀርባለው፡፡

PicsArt_1467544695260

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *