ወልዋሎ 3 ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ እንዲጫወት ቅጣት ተጣለበት

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አዲግራት ላይ መቀለ ከተማ ከ ፋሲል ከተማ ጋር ባደረጉት የከፍተኛ ሊግ 22ኛ ሳምንት ጨዋታ የተከሰተውን ረብሻ ተከትሎ ጥፋተኛ ነው ያለው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ላይ የገንዘብ እና በሜዳው ጨዋታ እንዳያደርግ ቅጣት ጥሎበታል፡፡

በጨዋታው በርካታ የወልዋሎ ደጋፊዎች የክለቡን ስም በመጥራት የፋሲል ከተማ ተጫዋቾች እና ደጋፊዎች ላይ ጉዳት ለማድረስ በመሞከራቸው ፣ ዛቻ በመሰንዘራቸው እና ክለቡም በዚህ አመት የዲስፕሊን ግድፈት ሪኮርዶች ያሉበት በመሆኑ ቅጣት መጣሉን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

በውሳኔው መሰረት በሜዳው የሚያደርጋቸውን ቀጣይ 3 ጨዋታዎች በገለልተኛ ሜዳ እንዲያደርግ ፣ 30,000 ብር እንዲቀጣ እና ለደጋፊዎቹ የስፖርታዊ ጨዋነት ትምህርት በመስጠት ሪፖርት እንዲያደርግ ተወስኗል፡፡

የውሳኔው ዝርዝር ይህንን ይመስላል፡-

PicsArt_1467711084320 PicsArt_1467711114548

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *