የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ጥሎ ማለፍ ወደ ፍፃሜው ምዕራፍ ተሸጋግሯል፡፡ ቅዳሜ በተካሄዱ ሁለት የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎችም ሀዋሳ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ለፍፃሜ አልፈዋል፡፡
ሀዋሳ ከተማ ከ አፍሮ ጽዮን ባደረጉት ጨዋታ መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 2-2 በሆነ አቸ ውጤት ሲፈጽሙ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጡት የመለያ ምቶች ሀዋሳ ከተማ 5-3 አሸንፏል፡፡
ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ ቡና ባደረጉት ጨዋታም በተመሳሳይ በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 2-2 አቻ ተለያይተው በተሰጡት የመለያ ምቶች ወላይታ ድቻ 4-2 በመርታት ወደ ፍጸሜው አልፏል፡፡
በሀዋሳ ከተማ እና ወላይታ ድቻ መካከል የሚደረገው የፍፃሜ ጨዋታ የት እና መቼ እንደሚደረግ ያልታወቀ ሲሆን አርብ ይታወቀል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ቡድኖቹ የፕሪሚየር ሊግ ማጠቃለያ ውድድራቸውን በአዳማ የሚያደርጉ በመሆናቸው ምናልባትም የጥሎ ማለፉ ፍፃሜ በአዳማ ሊካሄድ እንደሚችል ተገምቷል፡፡