ኮንፌድሬሽን ካፕ፡ ሁለቱ የሞሮኮ ክለቦች ዛሬ ይፋለማሉ

የ2016 ኦሬንጅ ካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ የምድብ ሶስተኛ መርሃ ግብር ዛሬ ማራካሽ ላይ በሚደረግ አንድ ጨዋታ ይጀመራል፡፡

በምድብ ሁለት አናት ላይ ያሉት ካውካብ ማራካሽ እና ፉስ ራባት ዛሬ የምድቡን መሪነት ለማጠናከር ይፋለማሉ፡፡ የ2015/16 የውድድር ዘመን የቦቶላ ሊግ አሸናፊው ፉስ ራባት ከሜዳው ውጪ ሶስ ቱኒዚያ ላይ ከ2015ቱ የኮንፌድሬሽን ካፕ አሸናፊው ኤቷል ደ ሳህል ላይ ወሳኝ የሆነ ነጥብ የወሰደ ሲሆን ከረጅም አመታት በኃላ ወደ ምድብ የተመለሰው ካውካብ ማራካሽ 100% የማሸነፍ ሪከርድ አለው፡፡

በሁለቱ ክለቦች መካከል ያለው የነጥብ ልዩነት ሁለት ብቻ መሆኑ እና ሁለቱም የሞሮኮ ክለቦች መሆናቸው ሲጨመርበት የጨዋታው ግለት ይጨምረዋል፡፡

በምድብ ሁለት የተደለደሉቱ ሁሉም ክለቦች ከሰሜን አፍሪካ ሲሆን ፉስ እና ካውካብ ወደ ግማሽ ፍፃሜው የማለፍ ተስፋቸው የጨመረ ይመስላል፡፡

ዓርብ ሰኔ 8/2008

03፡00 – ካውካብ አትሌቲክ ክለብ ማራካሽ (ሞሮኮ) ከ ፉት ዩኒየን ስፖርት ራባት (ሞሮኮ) (ግራንድ ስታደ ማራካሽ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *