በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ትላንት ሊደረግ የነበረው የወራቤ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ጨዋታ በጣለው ዝናብ ምክንያት ለዛሬ 04:00 መተላለፉ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን ዝናቡ እስከ ረፋድ በመቀጠሉና ሜዳው ባለመድረቁ ጨዋታው ሳይደረግ ቀርቷል፡፡
ጨዋታው ዛሬ እንዲካሄድ በወራቤ ከተማ በሚገኝ ሌላ ሜዳ ለማድረግ ቢሞከርም በተመሳሳይ በመጨቅየቱ ዋናው የወራቤ ሜዳ እስኪደርቅ ለመገበቅ ተገዷል፡፡ ሆኖም ሜዳው ባለመድረቁ ጨዋታው ለሌላ ጊዜ ተሸጋግሯል፡፡
በቀጣዮቹ ቀናት የወራቤ ሜዳ ሁኔታ ታይቶ ጨዋታውን ለማድረግ የማያስችል ከሆነ ጨዋታው በሀዋሳ አልያም ባቱ ሊደረግ ይችላል ተብሏል፡፡ ይህም ሁለቱ ክለቦች ከጅማ አባ ቡና እና ጂንካ ከተማ ጋር ሰኞ እንዲያደርጉ የወጣላቸው ተስተካካይ ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ እንዲሸጋገር ያደርገዋል፡፡
ሁለቱ ክለቦች በ3 ነጥቦች ልዩነት 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሲሆን ይህን ጨዋታ ሳይጨምር አዲስ አበባ ከተማ 3 ፣ ወራቤ ከተማ ደግሞ 1 ተስተካካይ ጨዋታ ይቀራቸዋል፡፡
ትላንት የተመዘገቡት ውጤቶች እና የደረጃ ሰንጠረዥ ይህንን ይመስላል፡-
ሀሙስ ሐምሌ 7 ቀን 2008
ምድብ ሀ
አክሱም ከተማ 1-1 ሰሜንሸዋ ደብረብርሃን
ወልድያ 2-1 ወሎ ኮምቦልቻ
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 1-2 ሙገር ሲሚንቶ
ኢትዮጵያ መድን 2-2 ሱሉልታ ከተማ
ቡራዩ ከተማ 0-1 ፋሲል ከተማ
ሰበታ ከተማ 2-1 አዲስ አበባ ፖሊስ
ምድብ ለ
ጅማ ከተማ 3-1 ሻሸመኔ ከተማ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 1-3 ጂንካ ከተማ
ነገሌ ቦረና 2-0 ባቱ ከተማ
ሀላባ ከተማ 1-0 ናሽናል ሴሚንቶ
ጅማ አባ ቡና 2-0 ፌዴራል ፖሊስ
ድሬዳዋ ፖሊስ 1-2 ደቡብ ፖሊስ
ያልተደረጉ ጨዋታዎች
አርሲ ነገሌ ከ ነቀምት ከተማ
(ለእሁድ ተሸጋግሯል)
አማራ ውሃ ስራ ከ ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት
(ለሌላ ጊዜ ተላልፏል )
ባህርዳር ከተማ ከ መቐለ ከተማ
(ለሌላ ጊዜ ተላልፏል)
ወራቤ ከተማ ከ አአ ከተማ
(ለሌላ ጊዜ ተላልፏል)