የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድር 4ኛ ቀኑን ይዟል፡፡ ዛሬ በምድብ ሀ በተደረጉ 2ኛ ጨዋታዎችም ሲዳማ ቡና ድል ሲቀናው ከፍተኛ ግምት አግኝቶ የነበረው ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
08:00 ላይ አዲስ አበባ ከተማን የገጠመው ሲዳማ ቡና 1-0 አሸንፏል፡፡ የሲዳማ ቡናን ብቸኛ የማሸነፍያ ጎል ከመረብ ያሳረፈው ፋሲል ዳግም ነው፡፡
10:00 ላይ የምድባቸውን የመጀመርያ ጨዋታ ያሸነፉት ሀዋሳ ከተማ እና ሐረር ሲቲ ተገናኝተው ያለ ግብ ጨዋታውን ፈጽመዋል፡
ከ2 ጨዋታዎች በኋላ የደረጃ ሰንጠረዦች ይህን ይመስላል፡-
የነገ ጨዋታዎች
08:00 ወላይታ ድቻ ከ ደደቢት
10:00 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ አዳማ ከተማ