U17 ፕሪሚየር ሊግ ማጠቃለያ ፡ አዳማ ከተማ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፉን አረጋግጧል

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድር በአዳማ አበበ ቢቂላ መካሄዱን ቀጥሏል፡፡ 5ኛ ቀኑን በያዘው ውድድር ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ደደቢት እና አዳማ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል፡፡

08:00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ ደደቢት ከፍፁም የጨዋታ ብልጫ ጋር ወላይታ ድቻን 2 -1 በማሸነፍ የምድቡን የመጀመርያ ድል አሳክቷል፡፡

የደደቢትን የድል ጎሎች ዳንኤል ግደይ እና የአብስራ ተስፋዬ ሲያስቆጥሩ የወላይታ ድቻን ብቸኛ ጎል ክብሩ በለጠ አስቆጥሯል፡፡

የደደቢቱ የአብስራ ተስፋዬ ጎል ከማስቆጠሩ በተጨማሪ በጨዋታው ላይ ባሳየው ድንቅ አቋም የተመልካቹን አድናቆት አትርፉል

PicsArt_1469036560938

10:00 በተካሄደው የእለቱ ሁለተኛ ጨዋታ አዳማ ከተማ ኢትዮ ንግድ ባንክን 2-1 በመርታት ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፉን አረጋግጧል፡፡

የአዳማን የድል ግቦች ኢሳ ንጉሴ እና የኋላሸት ፍቃዱ ሲያስቆጥሩ የንግድ ባንክን ብቸኛ ጎል ልዑል ኃይሉ አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ አደማ ከተማ በሰበሰበው ነጥብ ከምድቡ ከወዲሁ ለግማሽ ፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል፡

PicsArt_1469037109844

ውድድሩ ነገ ሲቀጥል በምድብ ሀ 08:00 ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሐረር ሲቲ ፤ 10:00 ላይ ሲዳማ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ ይጫወታሉ፡፡

 

ኮከብ ጎል አስቆጣሪዎች

3 የኋላሸት ፍቃዱ ( አዳማ ከተማ)

2 ኢሳ ንጉሴ (አዳማ ከተማ)

2 ዳንኤል ግደይ (ደደቢት)

2 ዮሐንስ ደረጄ (መከላከያ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *