አፍሪካ ፡ ቶታል የካፍ ውድድሮች ስፖንሰር ሆነ

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌድሬሽን (ካፍ) ግዙፉ የፈረንሳይ የነዳጅ ኩባንያ ቶታል ለስምንት አመታት ካፍን ስፖንሰር ማድረጉን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ቶታል የፈረንሳዩን የቴሌኮም ድርጅት ኦሬንጅን ተክቶ ካፍን ስፖንሰር ያደረገ ሲሆን የገንዘቡን መጠን ግን ከመግለፅ ኮንፌድሬሽን ታቅቧል፡፡

በ2017 ጋቦን የምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ ከወዲሁ የስያሜ ለውጥ ተደርጎበት የቶታል የአፍሪካ ዋንጫ የተባለ ሲሆን በካፍ ስር ያሉ ሌሎች 10 ውድድሮችም በቶታል ይሰየማሉ፡፡ በዚህም መሰረት የአፍሪካ ዋንጫ፣ ቻምፒየንስ ሊግ፣ ኮንፌድሬሽን ካፕ፣ ሱፐር ካፕ፣ ቻን፣ የወጣቶች ውድድሮች (ከ23 ዓመት፣ ከ20 ዓመት እና ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ)፣ የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ እና የአፍሪካ ፉትሳል ዋንጫ በቶታል ስም ይሰየማሉ፡፡ ካፍ በመግለጫው እንዳካተተው ከሆነ ስምምነቱ የአፍሪካ እግርኳስን በፈይናንስ ለመደገፍ ላቅ ያለ ድርሻ አለው፡፡

PicsArt_1469095346313

ካፍ ከ2009 ጀምሮ በኦሬንጅ ስፖንሰር የተደረገ ሲሆን ስምምነቱ ላለፉት ስምንት አመታት ቆይቷል፡፡ ኦሬንጅ የካፍ ውድድሮችን የስያሜ መብት አግኝቶ ስፖንሰር ያደረገ ሲሆን የ2016 ቻምቺየንስ ሊግ እና ኮንፌድሬሽን ካፕ በኦሬንጅ ስያሜ ለመጨረሻ ግዜ የሚደረጉ ይሆናሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *