ኤፍሬም አሻሞ ለደደቢት ለመፈረም ሲስማማ ታሪክ ጌትነት ውሉን አድሷል

ደደቢት የመስመር ተጫዋቹ ኤፍሬም አሻሞን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለማስፈረም መስማማቱን የክለቡ የቡድን መሪ አቶ ኪዳኔ ሀፍተፅዮን ይፋ አድርገዋል፡፡

የቀድሞው የሀረረ ቢራ የመስመር አማካይ ኤፍሬም አሻሞ በ2006 ክረምት ኢትዮጵያ ቡናን ለቆ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፈረመ ሲሆን ከ2 የውድድር ዘመናት በኋላ ደግሞ ደደቢትን በ2 አመት ኮንትራት ተቀላቅሏል፡፡

የኤፍሬም ለደደቢት መፈረም የአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ቡድን በመስመር ላይ ያለውን ክፍተት እንደሚደፍን ይጠበቃል፡፡

ኤፍሬም የሰማያዊዎቹ የመጀመርያ ፈራሚ ሲሆን ግብ ጠባቂው ታሪክ ጌትነትም ከክለቡ ጋር የሚያቆየውን ውል አድሷል፡፡ ደደቢት ተጨማሪ አጥቂ ከውጪ ለማምጣት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ታውቋል፡፡

ኄኖክ ካሳሁን ክለቡን ለቆ ወደ አዳማ ከተማ አምርቷል፡፡ ሳሚ ሳኑሚ እና ተካልኝ ደጀኔ ደግሞ ሌሎች ክለቡን ይለቃሉ የተባሉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡ ሳሚ ሳኑሚ ለሙከራ ውጪ ሀገር የሚገኝ ሲሆን ተካልኝ በውል ማደሻ ሂሳብ ባለመስማማቱ ክለቡን እንደሚለቅ ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *