የኢትዮዽያ ብሔራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር የምድብ ድልድል የእጣ ማውጣት ስነ ስርአት ዛሬ በባቱ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ተከናወኗለል፡፡
በስነስርአቱ ላይ የኢትዮጶያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ አባል እና የውድድር እና ስነስርአት ኮሚቴ ሃላፊ አቶ አሊሚራህ መሃመድ እንዲሁም የባቱ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ አሚኖ ናኒሶ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በስፍራው የተገኙ አመራሮችም መልክት አስተላልፈዋል፡፡
በተካሄደው የእጣ ማውጣት ስነስርአት ላይ በወጡት ደንቦች መሰረት ዕጣ አወጣጡ በየዞናቸው አንድ ምድብ የነበሩ እንዳይገናኙ ተደርጓል፡፡ (ይህ ከዞናቸው በጥሩ ሶስተኝነት ያለፉ ቡድኖችን አያካትትም)
በውድድሩ መጨረሻ የየዞናቸውን ውድድር በበላይነት ላጠናቀቁ ክለቦች እውቅና የሚሰጥ ሲሆን ለኮከብ አሰልጣኞች ፣ ተጫዋቾች እና ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ሽልማት ይበረከታል፡፡
የምድብ ድልድሉ ይህንን ይመስላል፡-
ከሀምሌ16 እስከ ነሐሴ 2 የሚቆየው ውድድር በባቱ ከተማ ሜዳና በሼር ኢትዮጵያ ስታድየም ይከናወናሉ፡፡
የመክፈቻ ጨዋታ
ነገ ሐምሌ 16 ቀን 2008
08:00 ወልቂጤ ከተማ ከ ደሴ ከተማ
(በባቱ ከተማ ስታዲየም)
* ሶከር ኢትዮዽያ እያንዳንዱን ጨዋታ እየተከታተለች ወደ እናንተ ታደርሳለች፡፡