የ2008 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር በባቱ (ዝዋይ) ከተማ ዛሬ በድምቀት ተጀምሯል፡፡
የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ አባላት አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ ፣ አቶ አሊሚራህ መሃመድ ፣ አቶ ነስረዲን መሀመድ ፣ የፅህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ወድምኩንን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በርካታ ቁጥር ባለው የስፖርት ቤተሰብ ታጅቦ ተጀምሯል፡፡
08:00 ላይ በተካሄደው የውድድሩ የመክፈቻ ጨዋታ የሰሜን ምዕራብ ዞን (ለ) ቻምፒዮኑ ደሴ ከተማ ከመካከለኛ ዞን (ለ) ቻምፒዮኑ ካለ ግብ በአቻ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቀዋል፡፡
ጨዋታው መልካም እንቅስቃሴ የታየበት ቢሆንም በተደጋጋሚ በሚሰሩ ጥፋቶች ምክንያት ጨዋታው እየተቆራረጠ ተመልካቹን ሲያሰለች ተስተውሏል፡፡
ውድድሩ ነገም ሲቀጥል በዚሁ ምድብ የሚገኙት አማራ ፖሊስ እና ሞጆ ከተማ 08:00 ላይ በባቱ ሜዳ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ በምድብ ለ 08:00 ላይ ዲላ ከተማ ከ ሚዛን አማን ፤ 10:00 ላይ አራዳ ክ/ ከተማ ከ ከቡታጅራ ከተማ ይጫወታሉ፡፡
ለማስታወስ ያህል የማጠቃለያ ውድድሩ የምድብ ድልድል ይህንን ይመስላል፡-