ብሄራዊ ሊግ ፡ ካፋ ቡና ወደ ሩብ ፍጻሜው ማለፉን ሲያረጋግጥ መተሃራ እና ዳባት ድል ቀንቷቸዋል

የኢትዮዽያ ብሄራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር የምድብ ሐ አና መ 2ኛ ጨዋታዎች ዛሬ ተከናውነው መተሃራ ፣ ዳባት እና ካፋ ቡና ድል ቀንቷቸዋል፡፡

08:00 ላይ በሼር ሜዳ መተሀራ ስኳር ከ ወሊሶ ከተማ ባደረጉት የምድብ ሐ ጨዋታ መተሃራ 1-0 አሸንፏል፡፡ የመተሀራ ሰኳርን ወሳኝ የድል ጎል ያስቆጠረው ፍሬው በቀለ ነው፡፡

ውጤቱን ተከትሎ መተሀራ ስኳር የማለፍ ተስፋውን ሲያለመልም በጥሩ 3ኝነት ለማጠቃለያው ያለፈው ወሊሶ ከተማ ከወዲሁ ከምድቡ ተሰናባች መሆኑን አረጋግጧል፡፡

በ10:00 ሼር ሜዳ ላይ እጅግ ጠንካራ ፉክክር ባስተናገደው ሌላኛው የምድብ ሐ ጨዋታ ካፋ ቡና ከ2-0 መመራት ተነስቶ 4-2 በማሸነፍ ከወዲሁ የሩብ ፍጻሜ ትኬቱን ቆርጧል፡፡

የካፋ ቡናን የድል ጎሎች አንተነህ ከበደ (2) ፣ ምንተስኖት ታረቀኝ እና አሊ አብደላ ሲያስቆጥሩ ቢንያም ጌታቸው እና ብሩክ ክንፈ የአምባሪቾን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል፡፡


የምድብ ሐ ሰንጠረዥ

ክለብ – ተጫ (ልዩነት) ነጥብ

1 ካፋ ቡና            2   (+3)  6

2 መተሃራ ስኳር    2   (+1)  4

3 አምበሪቾ          2   (-2)   1

4 ወሊሶ ከተማ    2   (-2)   0


08:00 ባቱ ሜዳ ላይ በለገጣፎ ከተማ እና ሽረ እንዳስላሴ መካከል ሊካሄድ የነበረው የምድብ መ ጨዋታ ሜዳው ውሃ በመያዙ እስኪስተካከል አንድ ሰአት ዘግይቶ 09:00 ሲጀምር ጨዋታውም ያለግብ ተጠናቋል፡፡

በመጀመርያው ጨዋታ መዘግየት ምክንያት 10:40 የተጀመረው የዳባት ከተማ እና ሶሎዳ አድዋ ጨዋታ በዳባት 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ኃይል የቀላቀለ አጨዋወት በታየበትና ሁለት ተጫዋቾች በቀይ ካርድ ከሜዳ በተወገዱበት ጨዋታ ተመስገን ምትኩ የዳባትን ብቸኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

PicsArt_1469726785978


የምድብ መ ሰንጠረዥ

ክለብ – ተጫ (ልዩነት) ነጥብ

1 ለገጣፎ ከተማ     2   (+1)   4

2 ሶሎዳ አድዋ        2   (0)     3

3 ዳባት  ከተማ       2   (0)     3

4 ሽረ እንዳስላሴ     2   (-1)   1


የመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ቦታ ፣ ሰአት እኛ ቀን ነገ የሚታወቅ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *