ብሄራዊ ሊግ ፡ አራዳ ክ/ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ ወደ ከፍተኛ ሊግ መግባታቸውን አረጋገጡ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ሁለት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ ሲደረጉ ወልቂጤ ከተማ እና አራዳ ክ/ከተማ ወደ ከፍተኛ ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

08:00 ላይ በተደረገው የመጀመርያ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ከ ዲላ ከተማ መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 2-2 አቻ አጠናቀዋል፡፡

ለወልቂጤ ከተማ ሚካኤል ወንድሙ እና ታሪኩ የኋላሸት ሲያስቆጥሩ ለዲላ ዳዊት ከበደ እና ኋላሸት ሰለሞን አስቆጥረዋል፡፡

አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የመለያ ምት ወልቂጤ ከተማ 5-4 በማሸነፍ ወደ ከፍተኛ ሊግ ማደጉን አረጋግጧል፡፡

ሙሉውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአስገራሚ ሁኔታ ቡድናቸውን በመደገፍ ለስታድየሙ ድምቀት የሆኑት የወልቂጤ ከተማ ደጋፊዎች ባቱ ከተማን በደስታ ሲያደምቋት አምሽተዋል፡፡

PicsArt_1470241306584

10:00 ላይ በተካሄደው ሁለተኛ ጨዋታ አራዳ ክፍለ ከተማ ከጨዋታ ብልጫ ጋር አማራ ፖሊስን 1-0 በማሸነፍ ወልቂጤ ከተማን ተከትሎ ወደ ከፍተኛ ሊግ መግባቱን አረጋግጧል፡፡

የአራዳ ክፍለ ከተማን ወሳኝ የድል ጎል ከእረፍት መልስ ዳዊት መኮንን አስቆጥሯል፡፡

PicsArt_1470241391109

በመካከለኛ ዞን ምድብ ለ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ ወደ ማጠቃለያው ያመሩት አራዳ እና ወልቂጤ ወደ ከፍተኛ ሊጉ ማለፍ ችለዋል፡፡

በዛሬው ጨዋታ የተሸነፉት ዲላ ከተማ እና አማራ ፖሊስ በነገው ጨዋታ ሽንፈት ከሚያስተናግዱት ሁለት ክለቦች ጋር በእጣ በድጋሚ ተጫውተው ካሸነፉ ወደ ከፍተኛ ሊጉ ያልፋሉ፡፡

የነገ ጨዋታዎች

08:00 መተሃራ ስኳር ከ ሽረ እንዳስላሴ (ባቱ ሜዳ)

10:00 ካፋ ቡና ከ ለገጣፎ ከተማ (ባቱ ሜዳ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *