ወልድያ እና አዲስ አበባ ከተማ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ዛሬ በተካሄዱት ጨዋታዎች ወልድያ እና አዲስ አበባ ከተማወደ ፕሪሚየር ሊግ ማደጋቸውን ያረጋገጡበትን ድል አስመዝግበዋል፡፡

መልካ ቆሌ ላይ ሙገር ሲሚንቶን ያስተነገደው ወልድያ ከመመራት ተነስቶ 2-1 በማሸነፍ 3 ጨዋታዎች እየቀሩት ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል፡፡

በ2007 ወደ ፕሪሚየር ሊግ አድጎ በዛው አመት ወደ ከፍተኛ ሊጉ የወረደው ወልድያ የፕሪሚየር ሊግ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን በቡድኑ ላይ በማከል በደጋሚ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለስ ችሏል፡፡

PicsArt_1470427336458
*ፎቶ – ከወልዲያ የፌስቡክ ገጽ የተወሰደ

10:00 ላይ ፌዴራልፖሊስን የገጠመው አአ ከተማ 2-0 በማሸነፍ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማለፉን ያረጋገጠ 4ኛው ክለብ ሆኗል፡፡

በ2003 የአዲስ አበባ 125ኛ አመት ክብረበአልን ምክንያት በማድረግ የተመሰረተው አዲስ አበባ ከተማ ከ5 አመት በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለማደግ የነደፈውን እቅድ በማሳካት ፕሪሚየር  ሊጉን ተቀላቅሏል፡፡

ከ2003 የውድድር ዘመን በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በ16 ክለቦች መካከል የሚደረገው የቀጣዩ የውድድር ዘመን ፕሪሚየር ሊግ ላይ ፋሲል ከተማ ፣ ጅማ አባ ቡና ፣ ወልድያ እና አአ ከተማ ፕሪሚየር ሊጉን የተቀላቀሉ ክለቦች ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *