የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሊጠናቀቅ ጥቂት ጨዋታዎች ቀርተውታል፡፡ ወደ ፕሪሚር ሊግ ያደጉት ክለቦች የተለዩ ሲሆን ቀሪዎቹ ጨዋታዎች ወደ ብሄራዊ ሊጉ የሚወርዱ 4 ክለቦችን ይለያሉ፡፡
ምድብ ሀ
ከዚህ ምድብ ቡራዩ ከተማ ፣ ሰሜንሸዋ ደብረብርሃን ፣ ሙገር ሲሚንቶ እና አክሱም ከተማ በተቀራረበ ነጥብ ተለያይተው ይገኛሉ፡፡ አክሱም 1 ፣ ሙገር 2 ቀሪ ጨዋታዎች የሚቀራቸው በመሆኑ ላለመውረድ በሚያደርጉት ትግል የተሸለ እድል ይዘዋል፡፡
የ4ቱ ክለብ ቀሪ ጨዋታዎች
13ኛ. ቡራዩ ከተማ – ከኢትዮጵያ መድን (ውጪ) እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ (በሜዳው)
14ኛ. ሰሜንሸዋ ደብረብርሃን – ከሙገር ሲሚንቶ (በሜዳው) እና ውሃ ስፖርት (ውጪ)
15ኛ. ሙገር ሲሚንቶ – ከሱሉልታ (ውጪ) ፣ አክሱም (በሜዳው) ፣ ባህርዳር ከተማ (ውጪ) ፣ ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን (ውጪ)
16ኛ. አክሱም ከተማ – ከሙገር (ውጪ) ፣ ሱሉልታ ከተማ (በሜዳው) ፣ ፋሲል ከተማ (ውጪ)
ምድብ ለ
ከዚህ ምድብ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመውረድ እጅጉን የተቃረበ ሲሆን ነቀምት ፣ ባቱ እና ፌዴራል ፖሊስ አብረው ላለመውረድ ተፋጠዋል፡፡
የ4ቱ ክለቦች ቀሪ ጨዋታዎች
13ኛ. ነቀምት ከተማ – ጅማ (በሜዳው) ፣ ደቡብ ፖሊሰ (ውጪ) ፣ አአ ከተማ (በሜዳው)
14ኛ. ባቱ ከተማ – ወራቤ (በሜዳው) ፣ ድሬዳዋ ፖሊስ (ውጪ) ፣ ጅማ ከተማ (በሜዳው)
15ኛ. ፌዴራል ፖሊስ – አአ ዩኒቨርሲቲ (በሜዳው) ፣ አርሲ ነገሌ (ውጪ) ፣ ወራቤ ከተማ (በሜዳው)
16ኛ. አአ ዩኒቨርሲቲ – ፌዴራል ፖሊስ (ውጪ) ፣ ጅማ አባ ቡና (በሜዳው) ፣ ሀላባ ከተማ (ውጪ)