በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የተዘጋጁትን ከ17 አመት በታች ውድድሮች በማሸነፍ ስኬታማ የውድድር ዘመን ያሳለፈው ሀዋሳ ከተማ ትላንት በሴንትራል ሆቴል ለቡድኑ አባላት የማበረታቻ ሽልማት አበርክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ደቡብ-ምስራቅ ዞን እና የማጠቃለያ ውድድሩን እንዲሁም የጥሎማለፉን በበላይነት ላጠናቀቁት የቡድኑ ተጫዋቾች በየደረጃው ለያንዳንቸው ከ4,000-5000 ብር የተበረከተላቸው ሲሆን ለአሰልጣኝ ተመስገን ዳና የ 5500 እንዲሁም ለረዳታቸው እስራኤል ጊና 5000 ብር ፣ ለህክምና ባለምያው ዘሪሁን ዳዊት 4500 ብር እና ለቡድን መሪው ጠሀ አህመድ 4500 ብር ተበርክቶላቸዋል፡፡
ከ100ሺህ ብር በላይ ወጪ በተደረገበትን የማበረታቻ ሽልማት ያበረከቱት የሀዋሳ ከተማ ም/ከንቲባ እና የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ ታምሩ ታፌ እና የሀዋሳ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ሀላፊና የክለቡ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ታሪኩ ኡጋሞ ናቸው፡፡