በ2017 ማዳጋስካር ለምታስተናግደው ከ17 አመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ ግብፅን ድሬዳዋ ላይ ታስተናግዳለች፡፡
የግብጽ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን 31 የልኡካን ቡድን በመያዝ ማለዳ ድሬደዋ የደረሰ ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደር ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ ዛሬ አመሻሽ ላይም ቀለል ያለ ልምምዱን ሰርቷል፡፡
ግብፅ በመጀመርያው ጨዋታ ካይሮ ላይ የደረሰባትን አስደንጋጭ የ3-1 ሽንፈት ለመቀልበስ አልማ ወደ ሜዳ ትገባለች፡፡
የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የሁለቱንም ቡድኖች የልዑካን ቡድን የእንኳን ደህና መጣቹ የእራት ግብዣ በራስ ሆቴል አመሻሹ ላይ አዘጋጅቷል፡፡
በተያያዘ የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ለእሁዱ ጨዋታ ልምምዱን ሲቀጥል ቋሚ ተሰላፊዎችን በመለየት የመከላከልና የማጥቃት ልምምዶችን ሰርተዋል፡፡ ከጉዳት ጋር በተያያዘ ሁሉም በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ታውቋል፡፡

በእሁዱ ጨዋታ ዙርያ የሁለቱንም ቡድኖች አሰልጣኞችና ተጨዋቾች ለሶከር ኢትዮዽያ የሰጡትን አስተያየት ነገ ይዘን የምንቀርብ መሆኑን ከወዲሁ እንገልፃለን፡፡