FT ፡ ኢትዮጵያ 2-1 ግብፅ
11′ 50′ አቡበከር ነስሩ
86′ ሃዚም ፋርጋሊ
ድምር ውጤት [5-2]
ተጠናቀቀ!!
ጨዋታው በኢትዮጵያ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ውጤት 5-2 በማሸነፍ ወደተከታዩ የማጣርያ ዙር አልፋለች፡፡ በቀጣዩ ዙርም የማሊ እና ቻድ አሸናፊን ይገጥማል፡፡
90+2′ ጫላ ተሺታ በድጋሚ መልካም የግብ አጋጣሚ አመከነ፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
88′ ሚኪያስ መኮንን ወጥቶ አክሊሉ አለሙ ገብቷል፡፡
ጎልልል!! ግብጽ
86′ ከ30 ሜትር አካባቢ የተሰጠውን ቅጣት ምት የኦኛ ስህተት ታክሎበት ሀዚም ፋርጋሊ አስቆጥሯል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
81′ ዳግማዊ አርአያ ወጥቶ ዳዊት ሳህሌ ገብቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ግብፅ
76′ መሃመድ አብድልጋኒ ወጥቶ አራቢ መሃመድ ገብቷል፡፡
71′ ግብፆች ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት ቢያደርጉም ጠንካራውን የኢትዮዽያ የተከላካይ መስመር ሰብረው መግባት አልቻሉም፡፡
69′ ዳግማዊ ከመስመር ያሻገረለትን ግልፅ የማግባት አጋጣሚ ጫላ ተሺታ አመከነው፡፡
የሚያስቆጭ አጋጣሚ!
የተጫዋች ለውጥ – ግብፅ
65′ ሀማዳ ዲፋላ ወጥቶ መሃመድ ሁሴን ገብቷል፡፡
64′ ሚኪያስ መኮንን በሚያደርገው ማራኪ እንቅስቃሴ የተመልካቹን ቀልብ እየሳበ ይገኛል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
60′ አምበሉ ማቲዎስ ወልደአረጋይ ባጋጠመው ጉዳት ወጥቶ ቃልኪዳን ዘላለም ገብቷል፡፡
53′ የኢትዮዽያ ብሄራዊ ቡድን ፍፁም አስገራሚ እንቅስቃሴ እያሳየ ይገኛል፡፡ በስታድየሙ የሚገኘው ተመልካችም ለቡድኑ ከፍተኛ ድጋፍ እየሰጠ ይገኛል፡፡
ጎልልል!!! ኢትዮጵያ
አቡበከር ናስር በድጋሚ አስቆጠረ፡፡ የሀረር ሲቲው አጥቂ ግብፅ ላይ በድምሩ 3 ግቦች አስቆጥሯል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ግብፅ
49′ አሚር መሃመድ ወጥቶ ረዳ አሊ ገብቷል፡፡
ተጀመረ!!!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀመረ፡፡
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በኢትዮጵያ መሪነት ተጠናቋል፡፡
ተጨማሪ ደቂቃ
የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 1 ቂቃ ተጨምሯል፡፡
ቢጫ ካርድ
40′ አምበሉ ማቲያስ ወልደአረጋይ አደገኛ ፋውል በመስራቱ የቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡
ቢጫ ካርድ
35′ ረመዳን የሱፍ ከኢትዮዽያ በኩል የመጀመርያውን የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
34′ ሙስጣፋ ጎዚ ከርቀት ወደ ጎል የመታውን ኳስ ኦኛ በግሩም ሁኔታ አዳነው፡፡
30′ የሜዳው አለመመቸት ሁለቱም ቡድኖች በሚፈልጉት መልኩ መጫወትና የፈለጉትን ታክቲክ መተግበር እንዳይችሉ የፈተናቸው ይመስላል፡፡
ቢጫ ካርድ
23′ መሃመድ ቶልባ የመጀመርያውን የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
18′ ጎሉ ከተቆጠረ በኋላ በሁለቱም ቡድኖች በኩል የተቀዛቀዘ ጨዋታ እየተመለከትን እንገኛለን፡፡
ጎልልል!!! ኢትዮጵያ
11′ አቡበከር ነስሩ በጥሩ ቅብብል የተቀበለውን ኳስ በጥሩ አጨራረስ ወደ ጎልነት ቀይሮታል፡፡
5′ ግብፆች ጎል ለማስቆጠር ወደ ኢትዮጵያ ጎል ቀርበው እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡
ሙከራ
3′ ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ ጫላ ተሺታ አክርሮ መትቶ ለጥቂት በግቡ አናት ወጣበት፡፡
ተጀመረ!!!
ጨዋታው በኢትዮጵያ አማካኝነት ተጀመረ፡፡
09፡56 ቁጥሩ በርካታ የሆነ ተመልካች በድሬደዋ ስቴዲዮም የተገኘ ሲሆን በአሰልጣኝ መሰረት ማኒ የሚመራው የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች በስታድየሙ ታድመዋል፡፡
09:53 የሁለቱም የብሔራዊ መዝሙር እየተዘመረ ይገኛል፡፡
09:50 ሁለቱም ቡድኖች ወደ ሜዳ ገብተው ከክብር እንግዶች ጋር እየተዋወቁ ይገኛሉ
የኢትዮጵያ አሰላለፍ
12 ኦኛ ኦመኛ (ግብ ጠባቂ)
2 እዮብ አለማየሁ
3 ሳሙኤል ተስፋዬ
4 ጌታሰጠኝ ሸዋ
7 ሚኪያስ መኮንን
8 ማትያስ ወልደአረጋይ (አምበል)
10 ዳግማዊ አርአያ
11 አቡበከር ነስሩ
14 ጫላ ተሺታ
16 እሱባለው ጌታቸው
18 ረመዳን የሱፍ
ተጠባባቂዎች
1 ፋሲል ገብረሚካኤል (ግብ ጠባቂ)
5 አማኑኤል አዲሱ
6 ሎክ ፓውሊንሆ
9 ሃቢብ ከማል
13 አክሊሉ አለሙ
15 ዳዊት ሳህሌ
17 ቃልኪዳን ዘላለም
የግብፅ አሰላለፍ
1 ሙስጣፋ ሾቢር (ግብ ጠባቂ)
3 ሃማዳ ዲፋላ
4 መሃመድ ኤልሳኢድ
6 መሃመድ ሻውር
7 የሱፍ ኤልጋማርዊ (አምበል)
11 መሃመድ አብድልጋኒ
12 መሃመድ ሄጋዚ
14 ሙስጣፋ ጎዚ
17 አሚር መሃመድ
19 ሃዚም ፋርጋሊ
24 መሃመድ ቶልባ
ተጠባባቂዎች
5 መሃመድ ኤልናጋር
8 አራቢ መሃመድ
9 ዚያድ መሃመድ
10 መሃመድ ሁሴን
15 ረዳ አሊ
16 ኦማር ሞሳድ (ግብ ጠባቂ)
18 አምር ሳሌህ