በዝውውር ገበያው የተቀዛቀዘው ኤሌክትሪክ ወደ ቀድሞ ባህሉ የሚመለስ ይመስላል

በዘንድሮው ክረምት ከሌሎቹ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በተለየ ኤሌክትሪክ እስካሁን የዝውውር ገበያው ላይ ተሳትፎ አላደረገም፡፡

ክለቡ ተጫዋቾችን በማሰናበት የተጠመደ ሲሆን በርካታ ተጫዋቾች ከወጣት ቡድኑ እንደሚያድጉ ይጠበቃል፡፡

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ክለቡን የተቀላቀለው ፍፁም ገብረማርያም ለተጨማሪ አንድ አመት ውል ያደሰ ሲሆን ሌሎች ውላቸው የተጠናቀቀ ተጫዋቾች ውል ሳይታደስላቸው ቀርቷል፡፡

አልሳዲቅ አልማሂ ፣ ማናዬ ፋንቱ ፣ አማረ በቀለ ፣ ማንኮ ክዌሳ ፣ አሰግድ አክሊሉ እና ፒተር ኑዋዲኬን ጨምሮ 9 ተጫዋቾች ክለቡን መልቀቃቸው ተረጋግጧል፡፡

እስካሁን ምንም ተጫዋች ያላስፈረመው ኤሌክትሪክ 11 ተጫዋቾችን ከተስፋ እና 17 አመት በታች ቡድኑ በማሳደግ ለቅድመ ውድድር ዝግጅት ወደ ሀዋሳ ያመራ ሲሆን ጥሩ አቋም የሚያሳዩትን በቋሚነት ወደ ዋናው ቡድን ይቀላቅላል፡፡ በቀጣዮቹ ጊዜያት ተጫዋቾች የማያስፈርም ከሆነም ከ1990ዎቹ አጋማሽ በኋላ ከወጣት ቡድኑ በርካታ ተጫዋች የማሳደግ ባህሉን ትቶ የቆየው ኤሌክትሪክን በአዲስ ገፅታ የምንመለከተው ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *