የነሀሴ 20 ምሽት አጫጭር የዝውውር ዜናዎች

ኢትዮጵያ ቡና ሳሙኤል ሳኑሚን የግሉ አድርጓል

ኢትዮጵያ ቡና ናይጄርያዊው አጥቂ ሳሙኤል ሳኑሚን ማስፈረሙን በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ይፋ አድርጓል፡፡

ከደደቢት ጋር ያለውን ውል ማጠናቀቁን ተከትሎ ከተለያዩ ክለቦች ዝውውር ጋር ስሙ ሲያያዝ የቆየው የ2007 የፕሪሚየር ሊጉ ከፍተኛ ግብ አግቢ የ2 አመት ኮንተትራት ፈርሟል፡፡

ወላይታ ድቻ ወንድወሰን ገረመውን አስፈርሟል

ወላይታ ድቻ በኢትዮጵያ ቡና የተለቀቀው ግብ ጠባቂው ወንድወሰን ገረመውን አስፈርሟል፡፡ የወንድወሰን ለድቻ መፈረም ድንቅ አመት ላሳለፈው ወንድወሰን አሸናፊ ሽፋን የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ሀዲያ ሆሳእና ጳውሎስ ጌታቸውን አሰልጣኝ አድርጎ ቀጥሯል

ከፕሪሚየር ሊጉ የወረደው ሀዲያ ሆሳእና አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸውን ዋና አሰልጣኝ አድሮጎ ሾሟል፡፡ የደሴ ከተማ አሰልጣኝ የነበረው እዮብ ማሀ “አሞካቺ” የጳውሎስ ረዳት ሆኗል፡፡

ደደቢት ለበርካታ ምእራብ አፍሪካዊያን የሙከራ አድል ይሰጣል

ደደቢት ከጋና እና ካሜሮን 14 ተጨዋቾችን የሙከራ እድል ሰጥቷቸዋል፡፡ሁሉም ተጫዋቾች የሙከራ ጊዜ ወጪያቸውን በራሳቸው በመሸፈን አዲስ አበባ እንደሚመጡ ለማወቅ ተችሏል፡፡

PicsArt_1472232686200

የዳዊት እስጢፋኖስ ማረፍያ ኤሌክትሪክ ሆኗል

ድሬዳዋ ከተማን የለቀቀው ዳዊት እስጢፋኖስ በመጨረሻም ለኤሌክትሪክ ለመፈረም ከስምምነት ደርሷል፡፡ የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና አምበል የኤሌክትሪክ የመጀመርያ ፈራሚ የሆነ ሲሆን የ1 አመት ኮንትራት ፈርሟል፡፡

ጅማ አባቡና ለቢያድግልኝ ፊርማ እየተንደረደረ ነው

ጅማ አባ ቡና የፕሪሚየር ሊጉ ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች ማሰሱን ቀጥሏል፡፡ ቢያድግልኝ ኤልያስን የግሉ ለማድረግም ጥረት እያደረገ ይገኛል

የአመለ ፣ እንዳለ እና ታደለ ጉዳይ አለየለትም

አመለ ሚልኪያስ ከአርባምንጭ ጋር በውል ማደስ ዙርያ እስካሁን ከስምምነት መድረስ አልቻለም፡፡ ለክለቡ ደውል ማደሻ ለመፈረም ተቃርበው እንደነበር የተነገረላቸው ታደለ መንገሻ እና እንዳለ ከበደ ጉዳይም እስካሁን እልባት አላገኘም፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ የተጫዋቾቹን ውል አድሷል

በዝውውር ገበያው የተቀዛቀዘው ቅዱስ ጊዮርጊስ የተጫዋቾቹን ውል በማደስ ላይ አተኩሯል፡፡ የክለቡ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ይፋ እንዳደረገው አሉላ ግርማ ፣ አዳነ ግርማ ፣  ምንተስኖት አዳነ ፣ ዘካርያስ ቱጂ ፣ መሃሪ መና እና ዘሪሁን ታደለ ውላቸውን ያደሱ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ፈረሰኞቹ ከምዕራብ አፍሪካ ተጫዋቾችን ለማስፈረም እየተንቀሳቀሱ ሲሆን 4 የተስፋ ቡድን ተጫዋቾችን አካተው በቢሾፍቱ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡

አአ ከተማ ሁለት ተጫዋቾች አስፈርሟል

ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደገው አአ ከማ የአዳማው ተከላካይ ዲሚጥሮስ ወልደሰላሴ እና በሱሉልታ ከተማ ድንቅ የውድድር ዘመን ያሳለፈው አጥቂው ኤርሚያስ ዳንኤልን አስፈርሟል፡፡ የዋና ከተማው ክለብ ሁለቱንም በ2 አመት ኮንንትራት ነው ያስፈረማቸው፡፡

አአ ከተማ ከኬንያ ሁለት ተጫዋቾችን ያመጣ ሲሆን በሚያሳዩት አቋም ታይተው ይፈርማሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *