​ኮፓ ኮካ ኮላ ዛሬ በይፋ ሲከፈት የወንዶቹ ውድድርም ተጀምሯል

የኮፓ ኮካ ኮላ ከ15 አመት በታች የማጠቃለያ ውድድር የመክፈቻ ስነስርአት ዛሬ ረፋድ ተካሂዷል፡፡ 3 የወንዶች ጨዋታዎችም ተደርገዋል፡፡

የሰልፍ ትርኢት እና ንግግሮች የመክፈቻ ስነስርአቱ አካል የነበሩ ሲሆን የቢሾፍቱ ከተማ ኦዲት ቢሮ ሃላፊ አቶ ተስፋየ አበበ ፣ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጁነይዲ ባሻ ፣ የኮካ ኮላ ሽያጭ እና ማርኬቲንግ ማናጀር ሆበርት ሄርሜንያ ፣ የኮካ ኮላ ማርኬቲንግ ማናጀር በኢትዮጵያ ትዕግስት ቱፋ እና አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የመክፈቻ ንግግሮች አድርገዋል፡፡

PicsArt_1472320121715

ትላንት በሴቶች የተጀመረው ውድድር ዛሬ በወንዶቹ ቀጥሎ ሲውል ኦሮሚያ እና አፋር ድል ቀንቷቸዋል፡፡

05፡00 ላይ ኦሮምያ ከድሬዳዋ ያደረጉት ጨዋታ በኦሮምያ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ የኦሮምያን የድል ግብ አምበሉ ዮሃንስ ሀብታሙ ከርቀት የተገኘውን ቅጣት ምት በቀጥታ መትቶ አስቆጥሯል፡፡ በጨዋታው ግሩም እንቅስቃሴ ሲያሳይ የዋለው ልኡል ሰገድ አለማየሁ በ2ኛው አጋማሽ የተሰጠውን የፍጹም ቅጣት ምት ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡ አምና በተካሄደው የይድነቃቸው ተሰማ መታሰብያ ውድድር ላይ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ያጠናቀቀው ኄኖክ ወልደገብርኤልም ጥሩ እንቅስቃሴ አሳይቷል፡፡

PicsArt_1472320071836

07፡00 ላይ አማራ ከ ሀረሪ ያደረጉት ጨዋታ ያለግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ በጨዋታው ሁለቱ ቡድኖች እየተፈራረቁ የበላነት የወሰዱ ሲሆን አማራ ክልል ገኘውን የፍጹም ቅታት ምት ልኡልሰገድ አለማየሁ መትቶ ግብ ጠባቂው አቤል ፍጹም አድኖበታል፡፡ ፍፁም ከፍጹም ቅታት ምቱ በተጨማሪ ግብ ሊሆኑ የሚችሉ ኳሶችን በማዳን ኮከብ ሆኖ ውሏል፡፡

09፡00 ላይ አፋር በጋምቤላ ላይ ፍጹም የበላይነቱን አሳይቶ 4-0 አሸንፏል፡፡ ከአፋር የድል ግቦች መካከል አህመዲን መሃመድ በ30 እና 74ኛው ደቂቃ ሁለት ግቦች ሲያስቆጥር መሃመድ ሃሰን በ45ኛው ደቂቃ በግሩም ሁኔታ በቮሊ አስቆጥሯል፡፡ ናትናኤል ዋሲሁን የቀሪዋ ግብ ባለቤት ነው፡፡

ጋምቤላዎች በጨዋታው ይህ ነው የሚባል ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ ያላደረጉ ሲሆን የአምናዎቹ ባለድሎች አፋሮች በአንጸሩ ምርጥ እንቅስቃሴ አሳይተዋል፡፡ የአህመዲን ፍጥነት እና የመሃመድ ሀሰን ክህሎት ደግሞ በጨዋታው ላይ ጎልተው የታዩ ነበሩ፡፡

PicsArt_1472320035593

የነገ ፕሮግራሞች

ሴቶች

07፡00 ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከ ጋምቤላ (ቢሾፍቱ ስታድየም)

08፡00 ኢትዮ ሶማሌ ከ ደቡብ (ለምለም ተስፋ ት/ቤት)

09፡00 አማራ ከ ድሬዳዋ (ቢሾፍቱ ስታድየም)

10፡00 አፋር ከ ኦሮምያ (ለምለም ተስፋ ት/ቤት)

ወንዶች

06:00 አዲስ አበባ ከ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ (ለምለም ተስፋ ት/ቤት)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *