ኢትዮጵያ 2-1 ሲሸልስ
33′ ጌታነህ ከበደ 53′ ሳልሃዲን ሰዒድ | 20′ አቺሌ ሄንሪቴ
ጨዋታው ተጠናቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሲሼልስ አቻውን በጌታነህ ከበደ እና ሳልሃዲን ሰዒድ ግቦች 2-1 ማሸነፍ ችሏል።
90‘ የባከነ ሰዓት – 3 ደቂቃ
88′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
ጌታነህ ከበደ ወጥቷል፤
ዳዊት ፍቃዱ ገብቷል።
83′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
ሽመልስ በቀለ ወጥቷል፤
ኤልያስ ማሞ ገብቷል።
82′ ስዩም ተስፋዬ ከሳጥኑ ውስጥ ያገኘውን ኳስ ሞክሮ ግብ ጠባቂው አውጥቶታል።
81′ ሳልሃዲን ሰዒድ በግንባሩ የሞከረው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል።
76′ የተጫዋች ለውጥ – ሲሼልስ
ኢውጃህ ታምቦ ወጥቷል፤
ዳንኤል ማይሌት ገብቷል።
73′ ሳልሃዲን ሰዒድ ጥሩ የግብ ማግባት አጋጣሚ አግኝቶ በሚያስቆጭ ሁኔታ አምክኖታል።
68′ አብዱልከሪም መሐመድ ያሻማውን ኳስ ጌታነህ ከበደ ገጭቶ ወደ ውጪ ወጥቶበታል።
66′ ሽመልስ በቀለ ከሳጥኑ ውስጥ ወደግብ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ይዞታል።
59′ ኤፍሬም አሻሞ ከርቀት የመታው ኳስ ከግቡ አናት በላይ ወጥቷል።
53′ ጎል!!!
ሳልሃዲን ሰዒድ ፍፁም ቅጣት ምቱን ወደ ግብ ቀይሯል።
52′ የሲሼልሱ ግብ ጠባቂ ጂኖ ሜላንቴ በሳላዲን ሰዒድ ላይ በሰራው ጥፋት የፍፁም ቅጣት ምት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተሰጥቷል።
49′ ጌታነህ ከበደ ግብ ቢያስቆጥርም ከጨዋታ ውጪ በሚል ተሽሯል።
48′ አብዱልከሪም መሐመድ ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ኳስ ሞክሮ ግብ ጠባቂው መልሶታል።
የተጫዋች ለውጥ – ኢተዮጵያ
ሽመክት ጉግሳ ወጥቷል፤
በሃይሉ አሰፋ ገብቷል።
ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሯል።

የመጀመሪያው አጋማሽ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።
45′ የባከነ ሰዓት – 2 ደቂቃ
38′ ሳላዲን ሰዒድ በግንባር የሞከረው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል።
33′ ጎል!!!
ጌታነህ ከበደ ከሳላዲን የደረሰውን ኳስ ወደ ግብ በመቀየር ኢትዮጵያን አቻ አድርጓል።
29′ ጌታነህ ከበደ በእጁ ግብ ለማስቆጠር በመሞከሩ ከዳኛው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል።
20′ ጎል!!!
አቺሌ ሄንሪቴ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ሲሼልስን መሪ አድርጓል።
16′ ጌታነህ ከበደ በሳጥኑ ውጪ ወደ ግብ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ይዞታል።
13′ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኳስን ተቆጣጥሮ በህብረት ወደ ግብ በመድረስ ሲሼልሶች ደግሞ በመልሶ ማጥቃት ለመጫወት እየሞከሩ ይገኛሉ።
5′ ጌታነህ ከበደ በግንባር የሞከረውን ኳስ ግብ ጠባቂው እንደምንም አውጥቶበታል።
10:06 ዩጋንዳዊው የመሐል ዳኛ ጨዋታውን አስጀምረዋል።
09:59 የኢትዮጵያ የብሔራዊ መዝሙር እየተዘመረ ይገኛል።
09:58 የሲሼልስ ብሔራዊ መዝሙር እየተዘመረ ይገኛል።
09:57 ሁለቱም ቡድኖች ወደ ሜዳ ገብተው ከክብር እንግዶች ጋር እየተዋወቁ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ አሰላለፍ
ጀማል ጣሰው
ስዩም ተስፋዬ (አምበል) – ሙጂብ ቃሲም – አንተነህ ተስፋዬ – አብዱልከሪም መሃመድ
ሽመክት ጉግሳ – ጋቶች ፓኖም – ሽመልስ በቀለ – ኤፍሬም አሻሞ
ሳላዲን ሰዒድ – ጌታነህ ከበደ
ተጠባባቂዎች
ተክለማሪያም ሻንቆ
ቴዎድሮስ በቀለ
መሃሪ መና
ኤልያስ ማሞ
አስራት መገርሳ
በሃይሉ አሰፋ
ዳዊት ፍቃዱ
የሲሼልስ አሰላለፍ
18 ጂኖ ሜላንቴ
2 ያኒክ ማኑ
5 ጆንስ ጁበርት
6 ቤኖይ ማሪ
7 ጄርቬይስ ዋዬ-ሂቬ
10 አቺሌ ሄንሪቴ
11 ካርል ሆፕሪች
12 ፋቢዮ ሌሚዬል
15 ኢውጃህ ታምቦ
17 ኮሊን ቢቢ
4 ጁድ ናንሲ
ተጠባባቂዎች
1 ኢያን አህኮንግ
13 ስቲቭ ኤስተር
14 ራያን አንታት
9 ብሌይን ሱዜት
16 ዳንኤል ማይሌት
3 አንድሪው ኦኔዚያ
8 ማይክ ሌስፔራንስ