የ2009 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚጀመርበት ቀን ለውጥ እንደተደረገበት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሸን አስታውቋል፡፡
ሊጉ ይጀመራል ተብሎ የወጣለት ቀን መስከረም 29/2009 ሲሆን አዲስ በወጣው ቀን መሰረት ጥቅምት 20 ቀን 2008 ይጀመራል፡፡ መስከረም 5 ሊወጣ የነበረው የእጣ ማውጣት ስነስርአትም ለጥቅምት 12 ተዛወሯል፡፡
ፌዴሬሽኑ ለቀኑ መራዘም በምክንያትያትነት ያስቀመጠው ወደ ፕሪሚየር ሊግ ያደጉት ፋሲል ከተማ ፣ ጅማ አባ ቡና ፣ አአ ከተማ እና ወልድያ የእረፍት እና የዝግጅት ጊዜ እጥረት እንደሚያጋጥማቸው በመግለፅ እንዲራዘም ጥያቄ በማቅረባቸው እንዲሁም ሜዳዎች ለጨዋታዎች ዝግጁ ባለመሆናቸው እንደሆነ ታውቋል፡፡
[socialpoll id=”2385802″]
[socialpoll id=”2385807″]