የሁለት ወር ደሞዝ ያልተከፈላቸው የአርባምንጭ ከተማ ተጫዋቾች ልምምድ አቋረጡ

አርባምንጭ ከተማ ለሁለት ወር የተጨዋቾችን የደሞዝ ክፍያ ባለመፈፀሙ ምክንያት ተጫዋቾቹ ልምምድ መስራት አቋርጠዋል፡፡

ተጫዋቾቹ የሐምሌ እና የነሐሴ ወር ደሞዛቸው ባለመለቀቁ ምክንያት ዛሬ ረፋድ ላይ ልምምዳቸውን ካከናወኑ በኋላ ደሞዛቸው እስኪከፈል ድረስ ልምምድ እንደማይሰሩ በመግለፅ አቁመዋል፡፡ ዛሬ 9:30 ላይ የነበረውን ልምምድም ሳይሰሩ መቅረታቸውን ሶከር ኢትዮዽያ ለክለቡ ቅርበት ካላቸው ምንጮቿ አረጋግጣለች፡፡

ሶከር ኢትዮዽያ ስለ ጉዳዩ ለማረጋገጥ ባደረገችው ጥረት የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ፀጋዬን አናግራ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

” አዎ የደሞዝ ክፍያው አልተፈፀመላቸውም፡፡ ያም የሆነበት ምክንያት ውላቸውን ያላደሱ ተጨዋቾችን ውል አድሰን ስንጨርስ አንድ ላይ ለመልቀቅ ስለታሰበ ነው፡፡ በቅርቡ የሚከፈላቸው ይሆናል፡፡ ” ሲሉ ስለ ጉዳዩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በአርባምንጭ ከተማ እንዲህ አይነት ችግር ሲያጋጥም ይህ የመጀመሪያ አይደለም፡፡ በውድድር ዘመኑ አጋማሽ ተጫዋቾች ደሞዝ ባለማግኘታቸው ልምምድ አቋርጠው እንደነበር አይዘነጋም፡፡



[socialpoll id=”2385802″]

[socialpoll id=”2385807″]

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *