የኢትዮዽያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከማሊ ጋር ላለበት ወሳኝ የማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅቱን በሀዋሳ እያደረገ ይገኛል፡፡
ከ17 አመት በታች ቡድኑ ከግብፅ ጋር የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታ ካደረገ በኋላ ለአንድ ሳምንት ዕረፍት በማድረግ ለተወሰኑ ቀናት በአአ ዝግጅት በማድረግ ከቆየ በኋላ አርብ ወደ ሀዋሳ በማቅናት ማረፊያውን ሴንትራል ሆቴል አድርጎ በተጠናከረ ሁኔታ በቀን ሁለት ጊዜ ልምምድ እየሰራ ይገኛል፡፡
ባሳለፍነው እሁድ ፍፃሜውን ካገኘው አራተኛው አገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና የምዘና ውድድር ላይ ጥሪ ከተደረገላቸው ከ10 በላይ ተጨዋቾች መካከል የMRI ምርመራውን በተሳካ ሁኔታ ያለፉት የደቡቦቹ ጃፋር ሙደሲ እና ምንተስኖት ዮሴፍ እንዲሁም የወላይታ ድቻው ፍቅረ ስላሴ ደሳለኝ እና የዲላ ከተማው ፋሲል አበባየሁ ከነገ ጀምሮ ከቡድኑ ጋር የሚቀላቀሉ ይሆናል፡፡
ብሄራዊ ቡድኑ ወደ ማሊ ከማቅናቱ በፊት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ከሱዳን አቻው ጋር ለማድረግ የተደረገው ጥረት ያልተሳካ ሲሆን በቀሩት ቀናት በሀዋሳ ከሚገኙ ቡድኖች ጋር ለማድረግ እንደታሰበ ለማወቅ ችለናል፡፡
የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ከማሊ ጋር የሚያደርገው የመጀመርያ ጨዋታ መስከረም 8 ማሊ ባማኮ ላይ ይደረጋል፡፡
[socialpoll id=”2385802″]
[socialpoll id=”2385807″]