ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት | 08-01-2009
ተጠናቀቀ | ኬንያ 3-2 ኢትዮጵያ
52′ 62′ ኔዲ አቴንዮ 74′ ካሮሊን አንያንጎ | 35′ 84′ ሎዛ አበራ
ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በኬንያ 3-2 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ሀራምቤ ስታርሌትስ ለ2016 የሴካፋ ዋንጫ ፍጻሜ አልፋለች፡፡
ተጨማሪ ደቂቃ
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዘዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
ጎልልል!!! ኢትዮጵያ
84′ ሎዛ አበራ ከብርቱካን ገብረክርስቶስ የተሻገረላትን ኳስ ተጠቅማ 2ኛ ግብ አስቆጥራለች፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
79′ መስከረም ካንኮ ወጥታ አትክልት አሸናፊ ገብታለች፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
78′ ህይወት ደንጊሶ ወጥታ እመቤት አዲሱ ገብታለች፡፡
ጎልልል!!!!
74′ ካሮሊን አንያንጎ ከቅጣት ምት የተሻማውን ኳስ በግንባሯ ገጭታ ከመረብ አሳርፋለች፡፡
72′ መዲና አወል ከብሩክታዊት የተሻገረላትን ኳስ ወደ ግብ ሞክራ ቋሚውን ታኮ ወጥቷል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
65′ ረሂማ ዘርጋ ወጥታ መዲና አወል ገብታለች፡፡
ጎልልል!!!
62′ ኔዲ አቴንዮ በድጋሚ ግብ አስቆጥራ ኬንያን መሪ ማድረግ ችላለች፡፡
ጎልልል!!!
52′ ኔዲ አቴንዮ ኬንያን አቻ ያደረገች ግብ ከመረብ አሳርፋለች፡፡
48′ ዌንደዲ አንቼንግ ከ18 ሜትር የመታችው ቅጣት ምት የግቡ አግዳሚ መልሶታል፡፡
ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
ዕረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በኢትዮጵያ መሪነት ተጠናቋል፡፡
ተጨማሪ ደቂቃ
የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ደቂቃ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኬንያ
44′ ቼሪስ ሳላኖ ወጥታ ኤልዛቤት አምቦጎ ገብታለች፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ኬንያ
40′ ዶረን ናብዊሬ ወጥታ ቪቪያን ኦዲያምቦ ገብታለች፡፡
ጎልልል!!!! ኢትዮጵያ
ሎዛዛዛዛ! ሎዛ አበራ ከህይወት ደንጊሶ የተቀቀለችውን ኳስ ተጠቅማ ኢትዮጵያን ቀዳሚ አድርጋለች፡፡ የሶከር ኢትዮጵያ የአመቱ ሴት የእግርኳስ ሰው አሸናፊ የሆነችው ሎዛ በውድድሩ 3ኛ ግቧን አስቆጥራለች፡፡
32′ ማሪ ዋንጂሩ የመታችው ቅጣት ምት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡
30′ ህይወት ደንጊሶ ከርቀት የሞከረችው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል
18′ ሽታዬ ሲሳይ የመታችውን ቅጣት ምት ሳማንታ በቀላሉ ይዛዋለች፡፡
14′ ኤሳ አኪዳ በግምት ከ18 ሜትር የመታችው ኳስ የግቡን አግዳሚ ለትሞ ተመልሷል፡፡
10′ እስካሁን በሁለቱም በኩል ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎች አላደረጉም፡፡
7′ ኔዲ አቴንዮ ከርቀት የሞከረችው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡
ተጀመረ!
ጨዋታው ተጀምሯል፡፡ ሩዋዳያን ዳኞች ጨዋታውን ይመራሉ፡፡
የኬንያ አሰላለፍ
12 ሳማንታ አኪንዪ
8 አን አሎች ኦንያንጎ (አምበል) – 15 ዌንዲ አን አቼንግ – 3 አይሪን አውሮር – 5 ዶርካስ ሺኮቤ
10 ካሮሊን አንያንጎ – 7 ቼሪስ ሳላኖ – 23 ዶረን ናብዊሬ
14 ኤሴ አኪዳ – 9 ኔዲ አቴንዮ – 4 ሜሪ ዋንጂኩ
ተጠባባቂዎች
1 ቪቪያን አኪንሂ ፣ 13 ኦኮ ካሌብ ፣ 14 ጃኪ ኦጎል ፣ 19 ሜርሲ አቼንግ – 16 ጃክሊን አኮት ፣ 17 ኤልዛቤት አምቦጎ ፣ 18 ቪቪያን ኦዲያምቦ
የኢትዮጵያ አሰላለፍ
1 ሊያ ሽብሩ
3 መስከረም ካንኮ – 4 ጥሩአንቺ መንገሻ – 5 ፅዮን እስጢፋኖስ – 17 እፀገነት ብዙነህ
12 ብሩክታዊት ግርማ – 14 ህይወት ደንጊሶ – 11 ብርቱካን ገብረክርስቶስ (አምበል)
10 ሽታዬ ሲሳይ – 7 ሎዛ አበራ – 9 ረሂማ ዘርጋ
ተጠባባቂዎች
21 ማርታ በቀለ ፣ 15 ፍቅርተ ብርሃኑ ፣ 16 ሰርካዲስ ጉታ ፣ 2 አትክልት አሸናፊ ፣ 8 መዲና አወል ፣ 6 እመቤት አዲሱ ፣ 16 አሳቤ ሙሶ
ይህን ጨዋታ የምናቀርብላችሁ ከልሳን ሴቶች ስፖርት ቀጥታ የሬድዮ ስርጭት እና ከተለያዩ ድረገጾች በምናገኘው መረጃ ነው፡፡