የኢትዮጵያ ከ17 እና ከ20 አመት በታች ሊጎች የሚጀምሩበት ቀናት ታወቁ

  የወጣቶች እግርኳስ | 13-01-2009 

የኢትዮጵያ እግርኳስ የ2009 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች እና ከ20 አመት በታች የሚጀመርባቸው ቀናትን ለክለቦች ይፋ አድርጓል፡፡

ዘንድሮ ለመጀመርያ ጊዜ ጊዜ የሚካሄደው የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ህዳር 18 ቀን 2009 እንዲጀመር ተወስኗል፡፡ የእጣ ማውጣት ስነስርአቱ ደግሞ ከአንድ ወር በፊት ጥቅምት 11 ቀን 2009 ይወጣል፡፡

በሊጉ የሚሳተፉት ክለቦች ብዛት ፣ ውድድሩ የሚደረግበት ፎርማት እና የትኞቹ ክለቦች ተሳታፊ እንደሆኑ እስካሁን በይፋ ያልተረጋገጠ ሲሆን ከጥቅምት 5 እስከ 30 ባለው ጊዜ በሚደረገው የክለቦች ምዝገባ መሰረት የሚሳተፉት ክለቦች የሚታወቁ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ አዲሱ የውድድር ዘመን ህዳር 11 ቀን 2009 ይጀምራል፡፡ የእጣ ማውጣት ስነ ስርአቱ ደግሞ ጥቅምት 8 ቀን 2009 ይካሄዳል፡፡

ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜ የሚካሄደው የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ላይ የሚሳተፉ ክለቦች ምዝገባ ከጥቅምት 1-20 እንደሚደረግ የታወቀ ሲሆን የተጫዋቾች የእድሜ ምርመራ ከመስከረም 25 እስከ ጥቅምት 30 የሚከናወን ይሆናል፡፡

የ2008 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ በሀዋሳ ከተማ አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *