በአአ ከተማ ዋንጫ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፉን አረጋግጧል

የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ሲቀጥሉ ቅዱስ ጊይሮጊስ ወደ ግማሽ ፍጻሜ የተሸጋገረበትን ድል አስመዝግቧል፡፡

09:00 ላይ ጅማ አባቡናን የገጠመው ቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 በማሸነፍ ከወዲሁ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፍ ችሏል፡፡ ፈረሰኞቹ ከጅማ አባ ቡና ፈተና ቢገጥማቸውም በጥሩ አቋም ላይ በሚገኘው አቡበከር ሳኒ ግብ 3 ነጥብ ይዘው ወጥተዋል፡፡ አቡበከር በ2 ጨዋታ 3 ግቦች በማስቆጠርየከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን መሪነት ጨብጧል፡፡

picsart_1477458718668

11:00 ላይ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከ መከላከያ ያደረጉት ጨዋታ 2-2 ተጠናቋል፡፡ ኤሌክትሪክ በአዲሱ አይቮሪኮስታዊ ፈራሚ ኢብራሂም ፋፋኖ ግብ ቀዳሚ ሲሆን ሳሙኤል ሳሊሶ መከላከያን አቻ አድድርጓል፡፡ ኤሌክትሪክ በሌላኛው ቡሩንዲያዊ አዲስ ፈራሚ ዲዲዬ ካቩምባጉ ግብ ወደ መሪነት ቢመለስም ተቀይሮ የገባው የተሻ ግዛው ጦሩን አቻ ማድረግ ችሏል፡፡

picsart_1477458774163

የምድብ ሀ ሰንጠረዥን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ6 ነጥብ ሲመራ መከላከያ በ2 ፣ ጅማ አባ ቡና እና ኤሌክትሪክ በ1 ነጥቦች ይከተላሉ፡፡

ውድድሩ ነገ ሲቀጥል ከምድብ ለ 09፡00 ላይ አዲስ አበባ ከተማ ከ ደደቢት ፣ 11፡00 ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ አዳማ ከተማ ይጫወታሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *