አአ ከተማ ዋንጫ ፡ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወደ ግማሽ ፍጻሜው አልፏል

የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ ሀ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ወደግማሽ ፍፃሜው ያለፈበትን ውጤትአስመዝግቧል፡፡

08፡00 ላይ ጅማ አባ ቡናን የገጠመው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ 2-1 በማሸነፍ ቅዱስ ጊዮርጊስን ተከትሎ ወደ ግማሽ ፍጻሜው አልፏል፡፡ ዳዊት እስጢፋኖስ እና ብሩክ አየለ የኤሌክትሪክን ግቦች ሲያስቆጥሩ ቴዎድሮስ ታደሰ የጅማ አባ ቡናን ግብ አስቆጥሯል፡፡ የኤሌክትሪክ ግቦች የተቆጠሩበት ሒደት ግሩም የነበረ ሲሆን የሄኖክ ግብ በድንቅነት የምትጠቀስ ነበረች፡፡

img_0517

10፡00 ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ ያደረጉት ጨዋ ያለግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ ጨዋታው እምብዛም ትኩረት ሳቢ ያልነበረ እና የግብ ሙከራዎች ያልታዩበት ነበር፡፡ መከላከያ ባደረጋቸው 3 ጨዋታዎች በሁሉም አቻ የተለያየ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ7 ነጥቦች የምድቡ የበላይ ሆኖ አጠናቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ምድብ ለ የመጨረሻ ጨዋታዎች ነገ ሲደረጉ 08፡00 ላይ አዳማ ከተማ ከ አዲስ አበባ ከተማ ፣ 10፡00 ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከደደቢት ይጫወታሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *