አአ ከተማ ዋንጫ ፡ አዳማ እና ንግድ ባንክ ወደ ግማሽ ፍጻሜ አልፈዋል

የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ትላንት ሲጠናቀቁ አዳማ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ግማሽ ፍጻሜው የተሸጋገሩበትን ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

08፡00 ላይ አዲስ አበባ ከተማን የገጠመው አዳማ ከተማ 2-1 በማሸነፍ ምድቡን በቀዳሚነት ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ በሁለቱ ጨዋታዎች የተጠቀመባቸውን አመዛኞቹ ተጫዋቾች አሳርፎ ወደ ሜዳ የገባው አዳማ ከተማ በበረከት ደስታ ግብ ቀዳሚ ሲሆን ዮናታን ብርሃኔ አዲስ አበባን አቻ ያደረገች ግብ በግንባሩ በመግጨት አስቆጥሯል፡፡ ተስፋዬ ነጋሽ በጥሩ ሁኔታ ከመሃል ሜዳ የተሸገረለትን ኳስ ተጠቅሞ በግሩም አጫራረስ አዳማን ለድል ያበቃች ግብ አስቆጥሯል፡፡

img_1005

10፡00 ላይ ደደቢት ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ጨዋታ በደደቢት 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ደደቢት ከምድቡ ለማለፍ በሁለት የግብ ልዩነት ማሸነፍ ይጠበቅበት የነበረ በመሆኑ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፍ ችሏል፡፡ ጥሩ እንቅስቃሴ እና ፉክክር በታየበት የመጀመርያው አጋማሽ ደደቢት አቤል ያለው እና ዳዊት ፍቃዱ ባስቆጠሯቸው ግቦች እስከ 73ኛው ደቂቃ ድረስ 2-0 ሲመሩ ቢቆዩም ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው ዳኛቸው በቀለ ያስቆጠራት ወሳኝ ግብ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግብ ልዩነት በልጦ ወደ ግማሽ ፍጻሜው እንዲያልፍ ረድታለች፡፡

img_0943

የግማሽ ፍፃሜው ጨዋታዎች ረቡዕ ሲካሄዱ 09፡00 ላይ አዳማ ከተማ ከ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ፤ 11፡00 ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይጫወታሉ፡፡ የጨዋታዎቹ አሸናፊዎችም በፍፃሜው እሁድ 10፡00 ላይ ይፋለማሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *