የሽመልስ በቀለ የመጨረሻ ደቂቃ ግብ ፔትሮጄትን ለድል አብቅቶታል

የግብጽ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ትላንት ሲጀመር ወደ አስዋን ያመራው ፔትሮጄት በሽመልስ በቀለ ግቦች ታግዞ ኤል ናስር ታዲን 2-1 አሸንፏል፡፡

በአስዋን ስታድየም በተደረገው ጨዋታ ሽመልስ በቀለ በ52ኛው ደቂቃ ፔትሮጄትን ቀዳሚ ሲያደርግ ፓትሪክ አዱ በ67ኛው ደቂቃ ኤል ናስርን አቻ ማድረግ ችሎ ነበር፡፡ ጨዋታው በዚሁ ውጤት ሊጠናቀቅ በተቃረበበት ሰአት ሽመልስ ከኦስማን መሃመድ የተሸገረለትን ኳስ በጥሩ ሁኔታ ተቆጣጥሮ የፔትሮጄትን ወሳኝ የማሸነፍያ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ድሉን ተከትሎ ፔትሮጄት መሪዎቹ ምስር ኤል ማቃሳ እና አል አህሊን ተከትሎ 3ኛ ደረጃ እንዲቀመጥ አስችሎታል፡፡ የምስር አል ማቃሳው አህመድ ኤልሼይክ በሚመራው የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ሰንጠረዥም ሽመልስ በቀለ በ3 ግቦች በማስቆጠር መካተት ችሏል፡፡

ሌላው ኢትዮጵያዊ ኡመድ ኡኩሪ የሚጫወትበት ኤንግ አል አረቢ በመጪው ቅዳሜ ከአል አህሊ ጋር የ9ኛ ሳምንት ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *