ዋልያዎቹ ከቻን መሰናበታቸውን አረጋገጡ

በመጀመርያው ጨዋታ በደካማ እንቅስቃሴ በሊቢያ የተሸነፈው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቀድሞዋ ሻምፒዮን ኮንጎ ብራዛቪል ተሸንፋ አንድ ጨዋta እየቀራት ከ2014 የቻን ውድድር መውጣቷን አረጋግጣለች፡፡ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ከመጀመርያው ጨዋታ 4 ለውጦችን አድርገው የገቡ ሲሆን ሳላዲን በርጊቾ ፣ አሉላ ግርማ እና ቢያድግልኝ ኤልያስ በመጀመርያው ጨዋታ ደክመው የነበሩትን ደጉ ፣ ስዩም እና አይናለምን ተክተው ገብተዋል፡፡ በአማካይ ክፍሉ ፋሲካ አስፋው ሲጨመር አጥቂው ዳዊት ፍቃዱ ከቋሚ አሰላለፍ ውጪ ሆኗል፡፡ ቡድኑ የቅርፅ እና የተጫዋች ለውጥ እንደማድረጉ የተሸለ ቢንቀሳቀስም አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው በሁለተኛው አጋማሽ የወሰዷቸው የተጫዋች ለውጦች ቡድኑ ወደ ቀድሞ ቅርፁ እንዲመለስ አስገድዶታል፡፡ ብዙም ሳይቆይ በ78ኛው ደቂቃ የተቆጠረባት ግብ ወደ ሩብ ፍፃሜ ለመግባት የነበራትን ተስፋ አሟጦታል፡፡

ከኢትዮጵያ ጨዋታ ቀደም ብሎ የተደረገው የሊቢያ እና ጋና ጨዋታ 1-1 ተጠናቋል፡፡ ምድቡን ሊቢያ እና ጋና በእኩል 4 ነጥብ ሲመሩ ኮንጎ በ3 ኢትዮጵያ ካለምንም ነጥብ ተከታዮችን ደረጃ ይዘዋል፡፡

{jcomments on}