መከላከያ ከ ኢትዮጵያ ቡና – ቀጥታ የጽሁፍ ስርጭት

መከላከያ2-2ኢትዮጵያ ቡና

65 ሚካኤል ደስታ ፣ 89 ማራኪ ወርቁ    |    54 ጋቶች ፓኖም (ፍ.ቅ.ም.) ፣ 71 ያቡን ዊልያም

 


ተጠናቀቀ

ጨዋታው 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡


90′ ዳኛው ተጨማሪ 4 ደቂቃ አሳይተዋል::


preview-copy89′ ጎል!!! መከላከያ!

ተመስገን ገብረፃዲቅ ያሻማውን ኳስ ማራኪርቁ በግንባሩ በመግጨት ዳግም መከላከያን አቻ አድርጓል፡፡


preview-copy-3

84′ የተጨዋች ለውጥ መከላከያ

ሽመልስ ተገኝ  ወጥቶ ቴዎድሮስ ታፈሠ ገብቷል፡፡


preview-copy-383′ የተጨዋች ለውጥ ኢትዮጵያ ቡና

አስቻለው ግርማ ወጥቶ ኢያሱ ታምሩ ገብቷል፡፡


preview-copy-380′ የተጨዋች ለውጥ ኢትዮጵያ ቡና

ኤልያስ ማሞ ወጥቶ ሳዲቅ ሴቾ ገብቷል፡፡

 

preview-copy-3የተጨዋች ለውጥ መከላከያ

ምንይሉ ወንድሙ ወጥቶ ተመስገን ገብረፃዲቅ ገብቷል፡፡


79′ አብዱልከሪም መሐመድ ከቀኝ መስመር የመታውን ኳስ ይድነቃቸው አውጥቶበታል፡፡


78′ መከላከያዎች በሳሙኤል ሳሊሶ አማካኝነት ያሻሙትን ቅጣት ምት ቴዎድሮስ ወርቁ ተቆጣጥሮ ወደግብ የሞከራትን ኳስ ዮሐንስ ሲተፋ በሃይሉ ግርማ ዳግም ሞክሮ የግቡ ቋሚ መልሶበታል፡፡


76′ ሚካኤል ደስታ የመታው ቅጣት ምት ለጥቂት ወደውጪ ወጥቷል፡፡


preview-copy-375′ የተጨዋች ለውጥ ኢትዮጵያ ቡና

ያቡን ዊልያም ወጥቶ አማኑኤል ዮሐንስ ገብቷል፡፡


preview-copy71′ ጎል!!! ኢትዮጵያ ቡና!

ያቡን ዊልያም በቅድሚያ ኤልያስ ማሞ የመታውን ኳስ የመከላከያው ግብ ጠባቂ ይድነቃቸው የተፋውን ተንሸራቶ አስቆጥሯል፡፡


preview-copy-367′ የተጨዋች ለውጥ መከላከያ

የተሻ ግዛው ወጥቶ ማራኪ ወርቁ ገብቷል


preview-copy65′ ጎል!!! መከላከያ!

ሚካኤል ደስታ በግንባሩ በመግጨት መከላከያን አቻ አድርጓል፡፡

 

preview-copy-563′ ሳሙኤል ሳኑሚ ይድነቃቸው ኪዳኔ ኳስ ሳይመታ በፊት ኳስ በመምታቱ በሁለተኛ ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል፡፡

 


61′ ሳሙኤል ታዬ በግራ በኩል ከየተሸ ግቅ 㝕ጸቀበላን ከዋስ ወደግብ ቢሞክርም ኳሷ ግን ከግቡ አናት በላይ ወጥታለች፡፡


58′ ኤልያስ ማሞ ለሳሙኤል ሳኑሚ በተከላካዮች መሃከል አሾልኮ ያቀበለውን ኳስ ሳኑሚ ቢሞክርም ይድነቃቸው አድኖበታል፡፡


57′ ጋቶች ፓኖም በግምት ከ35 ሜትር ርቀት አክርሮ የመታት ኳስ ለጥቂት ወደውጪ ወጥታለች፡፡


preview-copy54′ ጎል!!! ኢትዮጵያ ቡና!

ጋቶች ፓኖም የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡

 


53′ የመከላከያ ተጫዋቾች ፍፁም ቅጣት ምቱን በመቃወም ከዳኛው ጋር ሙግት ገጥመዋል፡፡


51′ ኢትዮጵያ ቡናዎች አስቻለው ግርማ የሞከረውን ኳስ በመከላከያተከላካዮች በእጅ በመነካትዋ ቡናዎች የፍፁም ቅጣት ምት አግኝተዋል፡፡


48′ አስቻለው ግርማ ከመከላከያ ግብ ክልል ውጪ አክርሮ የመታው ኳስ ኢላማውን ሳይጠብቅ ነቀርቶ ወደውጪ ወጥቷል፡፡


ተጀመረ!

ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀመረ::


እረፍትpreview-copy-7-copy-copy!!!

የመጀመሪያው አጋማሽ ያለግብ ተጠናቋል፡፡


45′ አስቻለው ግርማ ጭንቅላቱ በፋሻ ተጠቅልሎ ዳግም ወደሜዳ ገብቷል፡፡


43′ ያቡን ዊልያም በጭንቅላቱ ጨርፎ ያሳለፈለትን ኳስ ሳሙኤል ሳኑሚ ፍጥነቱን ተጠቅሞ ተከላካዮችን በማለፍ የሞከረውን ኳስ ይድነቃቸው በአስገራሚ ሁኔታ አድኖበታል፡፡


preview-copy-6-copy-copy41′ አስቻለው ግርማ ከሽመልስ ተገኝ ጋር ከኳስ ጋር አየር ላይ ሲጋጩ ጭንቅላቱ በመድማቱ የህክምና እርዳታ ለማግኘት ከሜዳ ወጥቷል፡፡

 


39′ አብዱልከሪም መሐመድ ያሻማውን ኳስ ሳሙኤል ሳኑሚ ከግብ ክልሉ ጠርዝ አካባቢ አግኝቶ ቢገጫትም ኳሳ ግን በቀላሉ ወደውጪ ወጥታለች፡፡


31′ አስቻለው ግርማ ሽመልስ ተገኝን በክርኑ ቢማታም ዳኛው ሁኔታውን ስላልተመለከቱ ጨዋታው ቀጥሏል፡፡


30′ ምንይሉ ወንድሙ ከቀኝ ክንፍ አቅጣጫ የተሻማለትን ኳስ በግሩም ሁኔታ ተቆጣጥሮ ቺፕ ለማድረግ ቢሞክርም ኳሷ ለጥቂት ወደውጪ ወጥታለች፡፡


preview-copy-5-copy29′ አስቻለው ግርማ ሳሙኤል ታዬ ላይ በሰራው ጥፋት ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡

 


26′ መከላከያዎች በፈጣን የመልሶ ማጥቃት ያገኙትን ኳስ ምንይሉ ወደግብ ቢሞክርም ዮሐንስ በዛብህ በቀላሉ አድኗታል፡፡


21′ የመከላከያው የቀኝ መስመር ተከላካይ ሽመልስ ተገኝ የሞከረውን ኳስ ዮሐንስ በዛብህ መልሶበታል፡፡ የተመለሰውን ኳሽ ምንይሉ ወንድሙ ዳግም ወደግብ ቢሞክርም ኳሷ ግን ኢላማዋን ሳትጠብቅ ወደውጪ ወጥታለች፡፡


preview-copy-5-copy14′ የኢትዮጵያ ቡናው ሳሙኤል ሳኑሚ በመከላከያ የግብ ክልል ውስጥ አስመስሎ በመውደቁ የጨዋታውን የመጀመሪያ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡

 


13′ አስቻለው ግርማ የግሉን ጥረት ተጠቅሞ ወደ መከላከያ ግብ ክልል ሰብሮ ከገባ በኋላ የሞከረው ኳስ ይድነቃቸው ኪዳኔ መልሶበታል፡፡


8′ ሳሙኤል ሳኑሚ መልካም የግብ ማስቆጠር አጋጣሚ ቢያገኝም ወደውጪ ወጥቶበታል፡፡


preview-copy-7-copy-copy

ጨዋታው ተጀመረ::

 


ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት በቅርቡ በድንገተኛአደጋ በሞት ለተለየው የሐዋሳ ከተማው ግብጠባቂ ክብረአብ ዳዊት የ1 ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል፡፡


የመከላከያ አሰላለፍ (4-4-2)

ይድነቃቸው ኪዳኔ

ሽመልስ ተገኝ — አዲሱ ተስፋዬ — ሚሊዮን በየነ — ቴዎድሮስ በቀለ

ሳሙኤል ሳሊሶ — በሃይሉ ግርማ — ሚካኤል ደስታ (አምበል) — ሳሙኤል ታዬ

የተሻ ግዛው — ምንይሉ ወንድሙ

ተጠባባቂዎች

አቤል ማሞ፣ ታፈሰ ሰርካ፣ ቴዎድሮስ ታፈሰ፣ ተመስገን ገብረፃዲቅ፣ መስፍን ኪዳኔ፣ ማራኪ ወርቁ፣ ኡጉታ ኦዶክ


የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ (4-3-3)

 

ዮሐንስ በዛብህ

አብዱልከሪም መሀመድ — ኤፍሬም ወንድወሰን — ኤኮ ፌቨር — አህመድ ረሽድ

 መስዑድ መሐመድ(አምበል) — ጋቶች ፓኖም — ኤልያስ ማሞ

አስቻለው ግርማ — ሳሙኤል ሳኑሚ — ያቡን ዊልያም

 

ተጠባባቂዎች

ጆቤድ ኡመድ ፣ አማኑኤል ዮሐንስ ፣ ኢያሱ ታምሩ፣ ወንድይፍራው ጌታሁን፣ አክሊሉ ዋለልኝ ፣ ዮሴፍ ዳሙዬ ፣ ሳዲቅ ሴቾ


preview-copy-7-copy

ጨዋታው ሊጀምር ደቂቃዎች ቀርተውታል፡፡ የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች ሜዳ ገብተው ሰውነታቸውን በማፍታታት ላይ ይገኛሉ፡፡

 


ሰላም ክቡራን የድረገጻችን ተከታታዮች! የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2009 የውድድር ዘመን ሁለተኛ ሳምንት የጨዋታ መርሃግብር ዛሬ እና ነገ በሚደረጉ 6 ጨዋታዎች የሚከናወን ይሆናል፡፡ በአዲስ አበባ ስታዲየም መከላከያ ከ ኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታም ዛሬ የሚደረግ ብቸኛው ጨዋታ ነው፡፡ ከዚህ ሰአት ጀምሮም ጨዋታውን የተመለከቱ መረጃዎች በዚሁ ገጽ ላይ እናቀርብላችኋለን፡፡

መልካም ቆይታ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *