የአዲስ አበባ ከተማ ውዝግብ እልባት አግኝቷል

የአዲስ አበባ ከተማ እግርኳስ ክለብ በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ለመሳተፍ መወሰኑን ለፌዴሬሽኑ በማሳወቅ ላለፉት ሁለት ሳምንታት የዘለቀው ውዝግብ እልባት አግኝቷል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ላይ እንደማይካፈል ማስታወቁን ተከትለ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በደንቡ መሰረት በውድድር ከተካተተ በኋላ ቡድን ማፍረስ እንደማይቻል በመግለጽ ክለቡን ከየትኛውም የፌዴሬሽኑ ውድድሮች እንደሚያግደው አስታውቆ ነበር፡፡ በዚህም መሰረት ክለቡ በነገው እለት በወንዶች ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ እንደማይካሄድ ለክለቦቹ በተጻፈ ደብዳቤ ተገልፆ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የክለቡ ቦርድ በተሰጠው ቀነ ገደብ 11ኛ ሰአት የሴቶች ቡድኑ ወደ ውድድር እንዲገባ መወሰኑን ለፌዴሬሽኑ ማሳወቁን ተከትሎ የነገውን ጨዋታ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡

የክለቡ ቦርድ ችግሩ የተፈጠረው በአሰራር ክፍተት መሆኑን አምኖ የማስተካከል እርምጃ እንደሚወስድ ለፌዴሬሽኑ በላከው ደብዳቤ አስታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *