ፕሪሚየር ሊግ ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአሸናፊነት ሲቀጥል ጅማ አባ ቡና በታሪክ የመጀመርያ ድሉን አስመዝግቧል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ተካሂደዋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአሸናፊነቱ ሲቀጥል ጅማ አባ ቡና በታሪክ የመጀመርያ ድሉን አጣጥሟል፡፡

አዲስ አበባ ላይ በ09:00 የተገናኙት ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና አዲስ አበባ ከተማ 1-1 አቻ ተለያይተዋል፡፡ የአአ ከተማ ዋንጫ አሸናፊዎቹ ኤሌክትሪኮች በ21ኛው ደቂቃ ዳዊት እስጢፋኖስ ባስቆጠረው ግብ ቀዳሚ መሆን ቢችሉም ፍቃዱ አለሙ አዲሱን የሊግ ክለብ በ39ኛው ደቂቃ አቻ ማድረግ ችሏል፡፡

img_0098

መልካ ቆሌ ላይ ደደቢትን ያስተናገደው ወልድያ ያለግብ አቻ ተለያይቷል፡፡ ወልድያ በ3 ጨዋታ መረቡን ሳያስደፍር በመውጣት መልከም አጀማመር ማድረግ ችሏል፡፡

ጅማ ላይ ጅማ አባ ቡና በታሪኩ የመጀመርያውን የፕሪሚየር ሊግ ድል ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ አስመዝግቧል፡፡ ባለክህሎቱ አማካይ ዳዊት ተፈራ በ50ኛው ደቂቃ የጅማን የመጀመርያ ታሪካዊ ግብ ከርቀት በመምታት ሲያስቆጥር የአምናው የከፍተኛ ሊግ ከፍተኛ ግብ አግቢ አሜ መሀመድ 80ኛው ደቂቃ ላይ በተመሳሳይ ከፍጹም ቅጣት ምት ውጪ አክርሮ በመምታት ሁለተኛውን አክሏል፡፡

ሶዶ ላይ ከሳምንቱ ጠንካራ ጨዋታዎች አንዱ የነበረው ጨዋታ በወላይታ ድቻ እና አዳማ ከተማ መካከል ተካሂዶ በድቻ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ አላዛር ፋሲካ ከበዛብህ መለዮ የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ የድቻን ብቸኛ የአሸናፊነት ግብ በ8ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡና ድሬዳዋ ከተማን አስተናግዶ 1-0 አሸንፏል፡፡ አዲሱ ኬንያዊ ፈራሚ ሰንደይ ሙቱኩ በ80ኛው ደቂቃ የሲዳማን ወሳኝ የማሸነፍያ ግብ አስቆጥሯል፡፡ በጨዋታው 6ኛ ደቂቃ አዲስ ግደይ በራሱ ላይ የተሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተሰጠውን የፍጹም ቅጣት ምት መትቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

15194341_1356276137745292_8893985672284562938_o

ሀዋሳ ከተማ የውድድር ዘመኑ የመጀመርያ ድሉን አርበምንጭ ከተማን 2-0 በማሸነፍ አስመዝግቧል፡፡ ከመከላከያ ክለቡን የተቀላቀለው ፍሬው ሰለሞን ሁለቱንም የሀዋሳ የድል ግቦች ከመረብ አሳርፏል፡፡ በጨዋታው የሀዋሳ ደጋፊዎች ባለፈው ሳምንት በ24 አመቱ በእሳት አደጋ ህይወቱ ያለፈው ክብረአብ ዳዊትን 24ኛው ደቂቃ ላይ ቆመው በማጨብጨብ አስበውት ውለዋል፡፡

img_0594

በ3ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ መከላከያን 3-0 አሸንፎ በምርጥ አጀማመሩ ቀጥሏል፡፡ ቡርኪናፋሷዊው አማካይ አብዱልከሪም ንኪማ በ56ኛው ደቂቃ ቀዳሚዋን ሲያስቆጥር ከ2 ደቂቃ በኋላ አዳነ ግርማ 3ኛ ተከታታይ የሊግ ግቡን አስቆጥሯል፡፡ በ80 ደቂቃ የተገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ሳላዲን ሰኢድ መትቶ የማሳረጊያዋነ ግብ አስቆጥሯል፡፡ በጨዋታው 37ኛ ደቂቃ መሀሪ መና በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ መሰናበቱነ ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ አመዛኙን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በ10 ተጫዋቾች ለመጫወት ተገዷል፡፡

ቅዳሜ በተደረገ ብቸኛ ጨዋታ ፋሲል ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን በኤርሚያስ ኃይሉ የ49ኛ ደቂቃ ግብ 1-0 አሸንፏል፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *