ሀዋሳ ከተማ በተጫዋቾቹ ላይ ቅጣት አስተላለፈ

ባሳለፍነው እሁድ በሀዋሳ ከተማ ስታድየም ሀዋሳ ከተማ ከ መከላከያ ጋር ሁለት አቻ በተለያዩበት የፕሪምየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ጨዋታ 3 ተጫዋቾች ከሀዋሳ ፣ 1 ተጫዋች ከመከላከያ በቀይ ካርድ ከሜዳ መሰናበታቸው ይታወሳል፡፡

ክለቡ ከጨዋታው በኃላ ባደረገው ግምገማ ያልተገባ ባህሪ ያሳዩት ተጫዋቾቹን መጠኑ በይፋ ያልተገለጸ ገንዘብ ቀጥቷል፡፡ በዲሲፕሊን ጥሰቱ ምክንያት ፌዴሬሽኑ የሚያስተላልፈውን የገንዘብ ቅጣት ተጫዋቾቹ እንዲከፍሉ ሲወሰን ዳግም ተመሳሳይ ግድፈት እንዳይፈጽሙም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ሀዋሳ ከተማ የእሁዱን ጨዋታ የዲሲፕሊን ግድፈት ተከትሎ አንበሎችንም ቀይሯል፡፡ ግርማ በቀለን ተክቶ የግራ ተከላካዩ ደስታ ዮሀንስ የክለቡ አዲስ አምበል ተደርጎ ሲመረጥ በእሁዱ ጨዋታ በተጠበባቂ ወንበር በፈጠረው ፀብ በቀይ ካርድ በተሰናበተው ሁለተኛው አምበል አዲስአለም ተስፋዬ ምትክ አዲሱ ፈራሚ ፍሬው ሰለሞን 2ኛ አምበል ሆኗል፡፡  አማካዩ ኃይማኖት ወርቁ ደግሞ በዳንኤል ደርቤ ምትክ 3ኛ አምበል ሆኗል፡፡

ሀዋሳ ከተማ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት ወደ ጎንደር አቅንቶ ፋሲል ከተማን ይገጥማል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *