ቀን ፡ እሁድ የካቲት 2 ቀን 2006 አም.
ስታዲየም ፡ አሚር አብዱላሂ ስታዲየም
የጨዋታ መጀመርያ ሰአት – 9፡00
በመጀመርያ የውድድር ዘመኑ በሲዳማ ቡና አስቸጋሪ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው በከፍተኛ ትምህርት ስፖርት ፌስቲቫል የደመቀችው ሐረርን የጎበኛል፡፡ በውዝግብ እየዳከረ የሚገኘው ሐረር ቢራ እና በወራጅ ቀጠና የሚገኘው ሲዳማ ቡና በተመሳሳይ ነጥብ ከደረጃ ሰንጠረዢ ወገብ በታች እንደመገኘታቸው መጠን ይህን ጨዋታ አሸንፈው ደረጃቸውን ለማሻሻል ከባድ ፍልሚያ ያደርጋሉ፡፡
ሁለቱም ክለቦች ለብሄራዊ ቡድኑ ምንም ተጫዋች ባለማስመረጣቸው ተጫዋቾቻቸው እረፍት ላይ የነበሩ ሲሆን እንደ ሲቲ ካፕ ባሉ ውድድሮች ላይ ባለመካፈላቸው ወቅታዊ አቋማቸው ምን እንደሚመስል መገመት ያስቸግራል፡፡
ጠቃሚ ነጥቦች
-ሐረር ቢራ በ6 ነጥቦች 11ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ እንግዳው ሲዳማ ቡና በተመሳሳይ ነጥብ በርካታ የግብ እዳ በመያዙ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
-ሲዳማ ቡና በ2002 ወደ ሊጉ ካደገ ወዲህ ሐረር ቢራን አሸንፈው አያውቁም፡፡
-አምና በተመሳሳይ ወቅት ሐረር ላይ ባደረጉት ጨዋታ ካለ ግብ አቻ ተጠናቋል፡፡
የእርስ በእርስ ግንኙነቶች
ተገናኙ – 8
ሐረር ቢራ አሸነፈ – 2
አቻ – 6
ሲዳማ ቡና አሸነፈ – 0
ሐረር ቢራ አስቆጠረ – 6
ሲዳማ ቡና አስቆጠረ – 4
{jcomments on}