በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና እና ሐረር ቢራ የአንደኛው ዙር የመጨረሻ ጨዋታቸውን ነገ ያደርጋሉ፡፡
በ25 ነጥቦች 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 8 ለማጥበብ የግድ ማሸነፍ የሚጠበቅበት ሲሆን በደረጃ ሰንጠረዡ 13ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ሐረር ቢራም ከወራጅ ቀጠና ለማምለጥ ቡናን ይፈትነዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ከሁለቱም ቡድኖች በኩል የወሳኝ ተጫዋቾች ጉዳት ለአሰልጣኞቹ ራስ ምታት ሆኖባቸዋል፡፡ በተለይም ሐረር ቢራ የነገውን ጨዋታ ካለ አምበሉ አቡበከር ደሳለኝ ፣ አጥቂው ልይህ ገብረመስቀል እና ተከላካዩ መግቢያነህ አሳዬን በጉዳት በረከት ገብረፃዲቅን ደግሞ ከክለቡ ጋር በገባው ውዝግብ ምክንያት ወደ ሜዳ ይገባል፡፡ ከኢትዮጵያ ቡና በኩል ደግሞ አምበሉ ዳዊት እስጡፋኖስ አይሰለፍም፡፡ ባለፉት ተከታታይ ጨዋታዎች ያልተሰለፈው ግብ ጠባቂው ጀማል ጣሰውም የመሰለፉ ጉዳይ አጠራጣሪ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ጨዋውን ለማሸነፍ እንደተዘጋጁ ሲገልፁ የሐረር ቢራው አቻቸው ኃይማኖት ግርማም ጨዋታውን አሸንፈው ለማንሰራራት እንዳለሙ ተናግረዋል፡፡
ከጨዋታው ቀደም ብሎ በኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ሊግ በ9፡00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መከላከያ ይጫወታሉ፡፡
{jcomments on}