ሀዋሳ ከነማ ታረቀኝ አሰፋን በዋና አሰልጣኝነት ሾመ

የሁለት ጊዜ የሊግ ሻምፒዮኑ ሀዋሳ ከነማ በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ስር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ያገለገሉት አሰልጣኝ ታረቀኝ አሰፋ ‹‹ ዳኜ ›› ን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል፡፡ በፕሪሚየርሊጉ ለ7 ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ የተሳናቸው አሰልጣኝ በፍቃዱ ዘሪሁን በአሰልጣኝ ታረቀኝ ስር ሆነው በምክትል አሰልጣኝነት እንዲሰሩ ክለቡ ወስኗል፡፡ አሰልጣኙ በፍቃዱ አምና የዘላለም ሽፈራው ምክትል ሆነው የሰሩ ሲሆን የ‹ሞውሪንሆ›ን መውጣት ተከትሎ ዋና አሰልጣኝ ሆነው ቢሾሙም በሀዋሳ ከነማ ውጤት ማምጣት ተስነኗቸው ወደ ቀድሞ ቦታቸው ተመልሰዋል፡፡

አሰልጣኙ ከሀዋሳ ከነማ ጋር የ2 አመት ኮንትራት የተፈራረሙ ሲሆን የደሞዛቸው መጠን ይፋ ባይሆንም ከፍተኛ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

አዲሱ አሰልጣኝ ታረቀኝ አሰፋ ለሀዋሳ ከነማ እና ለደቡብ እግር ኳስ አዲስ አይደሉም፡፡ በተጫዋችነት ዘመናቸው በ1990ዎቹ መጀመርያ ለሀዋሳ ከነማ የተጫወቱ ሲሆን በ2002 ሌላውን የደቡብ ክለብ ሲዳማ ቡና ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሳድገውታል፡፡ ‹ዳኜ› በአሰልጣኝነት በኒያላ ፣ ሰበታከነማ ፣ ሲዳማ ቡና እና ብሄራዊ ቡድን ለ10 አመታት የአሰልጣኝነት ልምድን አካብተዋል፡፡

{jcomments on}

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *