አዲስ አበባ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

FTአዲስ አበባ ከተማ 0-1ኢትዮጵያ ቡና

67′ ሳሙኤል ሳኑሚ


ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል።


89′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና

ኤልያስ ማሞ ወጥቶ አክሊሉ ዋለልኝ ገብቷል።


86′ እያሱ ታምሩ አማኑኤል ያሻገረውን ኳስ ከግብ ጠባቂው ጋር ተገናኝቶ ቢያገኘውም ደረጄ አውጥቶበታል።


80′ እሱባለው ሙሉጌታ ከርቀት የሞከረው ኳስ በቡና ተከላካዮች ተጨርፎ ወደውጪ ወጥቷል።


73′ ሳኑሚ ከሳጥኑ ውስጥ አግኝቶ ወደግብ የሞከረው ኳስ ወደላይ ወጥቷል።


67′ ጎል!!!!

አህመድ ረሺድ ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ ሳሙኤል ሳኑሚ በግንባሩ ገጭቶ በማስቆጠር ኢትዮጵያ ቡናን መሪ አድርጓል።


65 ‘ የተጫዋች ለውጥ – አዲስ አበባ ከተማ

ኤፍሬም ቀሬ ወጥቶ እሱባለው ሙሉጌታ ገብቷል።


64′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና

አብዱልከሪም ሀሰን ወጥቶ እያሱ ታምሩ ገብቷል።


62′ ኤልያስ ማሞ ከረጅም ርቀት ወደግብ የመታው ኳስ ለጥቂት ወደውጪ ወጥቷል።


61′ እንየው ካሳሁን ከሳጥኑ ውጪ የመታው ኳስ የግቡን ቋሚ ለትሞ ሲመለስ ኤፍሬም ቀሬ አግኝቶት በማይታመን ሁኔታ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።


59′ ጋቶች ፓኖም ከ30 ሜትር ርቀት ወደግብ አክርሮ የመታውን ኳስ ደረጄ አለሙ አውጥቶታል።


55′ ኢትዮጵያ ቡናዎች ከመጀመሪያው አጋማሽ በተሻለ ኳስን ተቆጣጥረው በቁጥር በርከት ብለው ወደግብ ለመድረስ እየሞከሩ ይገኛሉ።


50′ አስቻለው ግርማ የመታውን ኳስ ደረጄ አለሙ ሲተፋው ሳኑሚ በድጋሚ ወደግብ የመታውን ተከላካዮች ተደርበው መልሰውታል።


46′ ሁለተኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል።


የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና

ሳላምላክ ተገኝ ወጥቶ አህመድ ረሺድ ገብቷል።


የመጀመሪያው አጋማሽ ግብ ሳይቆጠርበት 0-0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።


45+1′ የመስመር ዳኛው ሳያሳዩ የመሀል ዳኛው አስቻለው ግርማ ከጨዋታ ውጪ አቋቋም ላይ ነው ብለው ውሳኔ በመስጠታቸው ከደጋፊዎች ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።


45′ ተጨማሪ ሰዐት – 2 ደቂቃ


40′ ሁለቱም ቡድኖች ግልፅ የግብ ዕድል ለመፍጠር ተቸግረዋል።


35′ ኤፍሬም ከኤልያስ ማሞ የተሰጠውን ኳስ በቀኝ መስመር በኩል ወደግብ ቢሞክርም ኳሱ ወደላይ ወጥቷል።


30′ ሳላምላክ ከመስመር ያሻማውን ኳስ ሳኑሚ በግንባሩ ሞክሮ ወደውጪ ወጥቶበታል።


25′ ፀጋ አለማየሁ በሃሪስተን ተጠልፏል በሚል የአዲስ አበባ ከተማ ተጫዋቾች ፍፁም ቅጣት ምት ስላልተሰጣው ተቃውሟቸውን ለዳኛው ገልፀዋል። ለሁለቱ ተጫዋቾች የህክምና ዕርዳታ ከተደረገላቸው በኃላ ጨዋታው ቀጥሏል።


22′ ኃይሌ እሸቱ ከግብ ጠባቂው ጋር ተገናኝቶ የመታውን ኳስ ሃሪስተን አውጥቶታል።


15′ አስቻለው ግርማ የኤልያስ ማሞን የማዕዘን ምት ተቀብሎ ይዞ በመግባት የመታው ኳስ ወደላይ ከፍ ብሎበት ወጥቷል።


10′ የተጫዋች ለውጥ – አዲስ አበባ ከተማ

ዮናታን ብርሃነ (በጉዳት) ወጥቶ ዘሪሁን ብርሃኑ ገብቷል።


3′ አብዱልከሪም ሀሰን በቮሊ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው በቀላሉ ይዞታል።


1′ ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡናው ሳሙኤል ሳኑሚ አማካኝነት ተጀምሯል።


የመጀመሪያ አሰላለፍ – አዲስ አበባ ከተማ

1 ደረጄ አለሙ

2 እንየው ካሳሁን – 20 ሰይፈ መገርሳ – 6 ጊት ጋትኮች – 81 አለማየሁ ሙለታ

10 ዮናታን ብርሃነ – 50 ፀጋ አለማየሁ – 30 ሙሃጅር መኪ – 90 አቤል ዘውዱ

24 ኤፍሬም ቀሬ – 8 ኃይሌ እሸቱ

የመጀመሪያ አሰላለፍ – ኢትዮጵያ ቡና

99 ሀሪሰን ሄሱ

18 ሣለአምላክ ተገኝ – 16 ኤፍሬም ወንድወሰን – 5 ወንድይፍራው ጌታሁን – 21 አስናቀ ሞገስ

25 ጋቶች ፓኖም

17 አብዱልከሪም ሀሰን – 9 ኤልያስ ማሞ – 8 አማኑኤል ዮሐንስ – 24 አስቻለው ግርማ

11 ሳሙኤል ሳኑሚ


09፡50 – ተጨዋቾቹ ወደመልበሻ ክፍል ገብተዋል።


09 ፡ 30 – የሁለቱ ቡድኖች ተጨዋቾች ሰውነታቸውን እያሟሟቁ ይገኛሉ ።


ሠላም እንደምን ውላችኋል ውድ አንባቢዎቻችን። በ13ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዲስ አበባ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና በአበበ ቢቂላ ስታድየም የሚያደርጉትን ጨዋታ እንደተለመደው በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት የጨዋታውን ዋና ዋና ክንውኖች የምናቀርብላችሁ ይሆናል።


መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *