የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 10ኛ ሳምንት 2ኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ሲካሄዱ ወልዋሎ እና መቀለ ከተማ ከተከታዮቻቸው በነጥብ የራቁበትን ፣ ጅማ ከተማ ደግሞ ወደ ምድቡ አናት የተመለሰበትን ድሎች ማስመዝገብ ችለዋል፡፡
ምድብ ሀ
ወደ ባህርዳር ያቀናው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 08:00 ላይ ባህርዳር ከተማን ገጥሞ 2-1 አሸንፏል፡፡ እዮብ ወልዋሎን ቀዳሚ ሲያደርግ ገናናው ባህርዳርን አቻ ማድረግ ችሎ ወደ እረፍት አምርተዋል፡፡ ከእረፍት መልስ ወልዋሎ በእንዳለ ግብ ታግዞ 2-1 ማሸነፍ ችሏል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ ወልዋሎ በ26 ነጥብ መሪነቱን ሲያጠናክር ባህርዳር ከወልዋሎ በነጥብ የሚቀራረብበትን እድል አምክኗል፡፡
ወደ ኮሞቦልቻ ያመራው መቀለ ከተማ ወሎ ኮምቦልቻን 1-0 በማሸነፍ ሁለተኛ ደረጃውን አጠናክሯል፡፡ ሳሙኤል መቀለ 3 ነጥብ ይዞ የተመለሰትን ግብ አስቆጥሯል፡፡
ለገጣፎ ለገዳዲ ሽረ እንዳስላሴን አስተናግዶ 1-0 በማሸነፍ ነጥቡን 11 አድርሶ ከወራጅ ቀጠናው መሸሽ ችሏል፡፡ ወደ ደብረብርሃን ያቀናው ሰበታ ከተማም ሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሃንን 1-0 በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠናው ወጥቷል፡፡
አማራ ውሃ ስራ ከ አራዳ ክፍለ ከተማ 1-1 አቻ ሲለያዩ አክሱም ከተማ ከ አአአ ፖሊስ ፖሊስ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ ተጠናቆ በዚህ ሳምንት ግብ ያልተቆጠረበት ብቸኛ ጨዋታ ሆኗል፡፡
በዚህ ምድብ ትላንት አበበ ቢቂላ ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ መድን ቡራዩ ከተማን 4-0 ሲረታ ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት ከ ሱሉልታ ከተማ 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ቀጣይ ጨዋታዎች
[table id=167 /]
[league_table 18186]
ምድብ ለ
እጅግ ከባድ ፉክክር እያስተናገደ በሚገኘው የከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ዛሬ በተካሄዱ 7 ጨዋታዎች የደረጃ ለውጦች ተከስተዋል፡፡
ካፋ ቡናን ያስተናገደው ጅማ ከተማ 1-0 በማሸነፍ የምድቡን መሪነት ከናሽናል ሴሜንት ተረክቧል፡፡ ጅማን 3 ነጥብ ያስጨበጠች ወሳኝ ግብ በሁለተኛው አጋማሽ ያስቆጠረው አስራት ቱንጆ ነው፡፡
ድሬዳዋ ላይ ናሽናል ሴሜንት ነቀምት ከተማን አስተናግዶ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡ ለ1 ሳምንት የተቀመጠበት 1ኛ ደረጃንም ለጅማ ከተማ አስረክቦ ወደ 2ኛ ደረጃ ወርዷል፡፡
ነገሌ ቦረና ሀላባ ከተማን አስተናግዶ 2-1 በማሸነፍ ወደ መሪዎቹ ፉክክር ተቀላቅሏል፡፡ ሀላባ በዘካርያስ ግብ ቀዳሚ መሆን ቢችልም በሃይሉ እና አንተነህ ያስቆጠሯቸው ግቦች ነገሌ ቦረናን ለድል አብቅተውታል፡፡
ጂንካ ከተማ ፌዴራል ፖሊስን 2-0 በማሸነፍ ደረጃውን አሻሽሏል፡፡ አርሲ ነገሌ በሀቲስ ብቸኛ ግብ 1-0 በማሸነፍ መሪዎቹን ተጠግቷል፡፡ ደቡብ ፖሊስ ደግሞ በአገኘው ልኬሳ ግብ ድሬዳዋ ፖሊስን 1-0 መርታት ችሏል፡፡
ወልቂጤ ከተማ ከ ሻሸመኔ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ሲጠናቀቅ በዲላ እና ሃድያ ሆሳዕና መካከል ሊካሄድ የነበረው ጨዋታ በርካታ የሃድያ ተጫዋቾች በመታመማቸው ምክንያት ለሌላ ጊዜ ተላልፏል፡፡
ምድብ ለ ከ10 ሳምንታት በኋላ በደረጃ ሰንጠረዡ ከፍተኛ የነጥብ መቀራረብ ሲስተዋል በመሪው ጅማ ከተማ እና 15ኛ ደረጃ ላይ በሚገኘው ነቀምት መካከል ያለው የነጥብ ልዩነት 9 ብቻ ነው፡፡
ቀጣይ ጨዋታዎች
[table id=168 /]
[league_table 18205]