ሐረር ቢራ እግርኳስ ክለብ በቅርቡ በባለሃብቶች እጅ ይገባል

በከፍተኛ የአስዳደር ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ሐረር ቢራ ከፋብሪካው አስተዳደር ተላቅቆ በባለሃብቶች ስር ሊሆን መቃረቡን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

ጋዜጣው እንደዘገበው የሀረር ባለሃብቶች ከ ፋብሪካው ጋር ባደረጉት ድርድር ክለቡ ወደ ወደ ባለሃብቶቹ ይዞታ ተጠቃሎ መጠርያ ስሙም ከሐረር ቢራ ወደ ሃረር ከተማ እንዲለወጥ ከስምምነት ደርሰዋል፡፡

ከ1995 ጀምሮ በፕሪሚየር ሊጉ እየተወዳደረ የሚገኘው ‹‹ ሐረር ከተማ ›› በደረጃ ሰንጠረዡ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ላለመውረድ እየታገለ ይገኛል፡፡

{jcomments on}

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *