​አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ በወልድያ ይቀጥላሉ

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከወልድያ ስፖርት ክለብ ለመልቀቅ የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተው የነበሩት አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ በክለቡ ለመቀጠል በመስማማታቸው የመልቀቅ ሀሳባቸውን ቀይረው በወልድያ እንደሚቆዩ ተረጋግጧል፡፡

አሰልጣኝ ንጉሴ ቡድኑ ወልድያ ወደ ጅማ ተጉዞ ጅማ አባ ቡናን ካሸነፉበት ጨዋታ በኋላ ከቡድኑ ጋር ወደ ወልድያ ሳይጓዙ በአዲስ አበባ ቆይተው የነበረ ሲሆን በዛሬው እለት በቡድኑ የእራት ፕሮግራም ላይ በድንገት ተገኝተው ከቡድኑ ጋር ተቀላቅለዋል፡፡

በ14ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ወልድያ በመሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ስታድየም ኢትዮ ኤሌክትሪክን በሚያስተናግድበት ጨዋታ ካለ አሰልጣኝ ወደ ሜዳ የመግባት ስጋት የነበረበት ቢሆንም ንጉሴ ደስታ በመመለሳቸው ቡድኑን እየመሩ የነገውን ጨዋታ ያከናውናሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *