ተጫዋቾቻችን ከሃገር ውጪ . . .

-ለአመታት በሁለቱ የኦምዱርማን ክለቦች የተያዘውን የበላይነት አህሊ-ሼንዲ መገዳደር ጀምሯል፡፡ ትላንት ምሽት በሱዳን ፕሪሚየር ሊግ አህሊ-አትባራን 1-0 ያሸነፈው አህሊ ሼንዲ ካለምንም ሽንፈት ሊጉን መምራት ጀምሯል፡፡ ኢትዮጵያውኑ አዲስ ህንፃ እና አብይ ሞገስም በቡድኑ ስኬት ላይ ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ነው፡፡ ሼንዲን በምክትል አሰልጣኝነት እያሰለጠኑ ያሉት የቀድሞው የፕሪሚር ሊግ ሻምፒዮን ውበቱ አባተም ቡድኑ ላመጣው ውጤት የምስጋና እና እውቅና ምስክር ወረቀት ከክለቡ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ከስነ-ስርአቱ በኋላ ውበቱ አባተ በተደረገላቸው ማበረታቻ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

-ትላንት ምሽት በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ ዋዲ ዴግላ በአል-ቃናህ 2-1 ሲሸነፍ ሳላዲን ሰኢድ በጉዳት ምክንያት ጨዋታው አምልጦታል፡፡ ሳላዲን በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ወደ ዛማሌክ አልያም ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊዛወር እንደሚችል መወራቱ ቢነገርም ለአፍሪካው ታላቅ ክለብ አል-አህሊ ሊፈርም መቃረቡን አምኗል፡፡

{jcomments on}

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *