የኢትዮጵያ ሴቶች ጥሎማለፍ ውድድር 2ኛ ዙር ጨዋታዎች ትላንት ተደርገው ወደ ሩብ ፍጻሜ ያለፉት 4 ክለቦች ታውቀዋል፡፡
አበበ ቢቂላ ላይ በ08:00 አዳማ ከተማ ከ ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ያደረጉት ጨዋታ በአዳማ 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ቀጥሎ በተደረገው ጨዋታ ደግሞ ጌዲኦ ዲላ በአስገራሚ ጉዞው በመቀጠል ልደታ ክፍለ ከተማን 5-1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል፡፡
አአ ስታድየም ላይ በ09:00 ሊካሄድ የነበረው የድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርተት አካዳሚ ጨዋታ ድሬዳዋ በቦታው ባለመገኘቱ ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡ ለአካዳሚም ፎርፌ ተሰጥቷል፡፡ ቀጥሎ በተካሄደው ጨዋታ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ቦሌ ክፍለከተማን 1-0 በማሸነፍ ሌላው ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀለ ቡድን ሆኗል፡፡
የ2ኛው ዙር ቀጣይ ጨዋታዎች የካቲት 21 ተካሂደው ወደ ሩብ ፍጻሜው የሚያልፉ ክለቦች ይለያሉ፡፡
2ኛ ዙር
የካቲት 17 ቀን 2009
ድሬዳዋ ከተማ 0-3 ኢ.ወ.ስ. አካዳሚ (ፎርፌ)
ቦሌ 0-1 ንፋስ ስልክ ላፍቶ
አዳማ ከተማ 3-1 ቅድስት ማርያም
ልደታ 1-5 ጌዲኦ ዲላ
ማክሰኞ የካቲት 21 ቀን 2009
09:00 ጥረት ከ ኢትዮጵያ ቡና (አአ ስታድየም)
11:30 ደደቢት ከ ሲዳማ ቡና (አአ ስታድየም)
08:00 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ አርባምንጭ ከተማ (አበበ
ቢቂላ)
10: 00 መከላከያ ከ ሀዋሳ ከተማ (አበበ ቢቂላ)