ኢትዮ ኤሌክትሪክ 0-0 ጅማ አባ ቡና | የአሰልጣኞች አስተያየት

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በአዲስ አበባ ስታድየም ጅማ አባ ቡናን ያስተናገደበት ጨዋታ 0 – 0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል ። የቡድኖቹ አሰልጣኞችም በጨዋታው ዙሪያ የነበራቸውን አስተያየት እንደሚከተለው ገልፀዋል ።

አሰልጣኝ ብርሀኑ ባዩ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ

” ጨዋታው ጥሩ ነበር ። በመጀመሪያው አጋማሽ ጅማ አባ ቡናዎች ጥሩ ነበሩ ። የጎል ዕድሎችንም ለመፍጠር ሞክረዋል ባይጠቀሙበትም ። በተቃራኒው ደግሞ እኛ  በሁለተኛው አጋማሽ በተለይም በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ለጎል የቀረቡ ዕድሎችን መፍጠር ችለናል ። በእንቅስቃሴም የተሻልን ነበርን ። የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ይዘን የገባነው ዕቅድ በአግባቡ ሊተገብሩልን ባለመቻላቸው በሁለተኛው ግማሽ ሁለት ተጨዋቾችን ቀይረናል ። ከዛ በኋላም የተሻለ መንቀሳቀስ ችለናል ። በቀላሉ ወደ ጎል የመድረስ አቅማችን አሁንም አብሮን ቢኖርም የግብ ዕድሎችን ማባከናችን ግን እንደቀጠለ ነው። ይህን ችግር ለመቅረፍ ያረግነው ጥረትም አልተሳካም። በቀጣይ በዚህ ችግራችን ላይ የምንሰራ ይሆናል ”

 አሰልጣኝ ገ/መድህን ኃይሌ – ጅማ አባ ቡና

” ጨዋታው በአጠቃላይ ጥሩ ነው። ከተቻለ ለማሸነፍ ካልሆነም እኩል ለመውጣት ነበር ሀሳባችን ። የምንፈልገውን ነጥብም አግኝተናል ዕቅዳችንም ተሳክቷል ማለት እችላለው ። በጥንቃቄ ነበር ለመጫወት የሞከርነው ። በእርግጥ ኤሌክትሪክ ወደመጨረሻ ላይ ተጭኖን ነበር ። የግብ ሙከራ በብዛት በማድረግ ግን እኛ የተሻልን ነበርን ። እንደሙከራችን ከሆነ እንደውም ማሸነፍ ይገባን ነበር ። ኤሌክትሪክ በልምድም ሆነ በተጨዋች ስብስብም ቢሆን ከኛ የተሻለ ነው ። ቢሆንም እንደቡድን ከዕድሜም አንፃር  ተጨዋቾቻችን የያሳዩት አቋም ከሚገባው በላይ ነው ማለት ይቻላል ። በተጨማሪ እስካሁን ሁለት አዲስ ተጨዋቾችን ነው ማግኘት የቻልነው ። ሊያውም አንደኛው ትላንት ነው የጀመረው ። በቀጣይ ከተቻለ ሌሎች ሁለት ተጨዋቾችን ጨምረን ካሉን ወጣት ተጨዋቾች ጋር በማካተት እንደ ቡድን የተሻለ ነገር ለመስራት እንሞክራለን ። “

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *